Fana: At a Speed of Life!

አሸባሪውን ህወሓት የሚያወግዝ ሰልፍ በጅግጅጋ ተካሄደ

 

አዲስ አበባ፣ጥቅምት 28፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አሸባሪውን እና የጥፋት ቡድን የሆነውን ህወሓት የሚያወግዝ ሰላማዊ ሰልፍ ዛሬ በጅግጅጋ ተካሄደ፡፡

በዚህ ሰላማዊ ሰልፍ ላይ ከሃያውም ቀበሌ የመጡ የጅግጅጋ ከተማ ነዋሪዎች እና የከተማ አስተዳደር አመራሮች ተገኝተዋል።

በ ሰላማዊ ሰልፉ ላይ ንግግር ያደረጉት የፋፈን ዞን አስተዳደር አቶ አብዲሐኪን መሐመድ አሸባሪው ቡድን ለሶስት አስር አመታት በሐገርና በክልሉ ላይ ያደረሰው ግፍና መከራ አልበቃ ብሎት ዛሬም ዳግም ህዝብና ሐገርን ለመበተን ከተለያዩ የጥፋት ቡድኖች ጋር ሐገር ለማፍረስ የሚያደርገውን ክፉ ስራ እንደሚያወግዙ እና በአንድነት መታገል አለብን ብለዋል ።

በሰልፍ ላይ የተገኙ የጅግጅጋ ነዋሪዎችም አሸባሪውን እና ሐገር አፍራሹን ቡድን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ለማጥፋት መንግስት የሚያደርገውን የህግ ማስከበር እርምጃ እስከ መጨረሻው እንደሚደግፉ ገልፀው ከሀገር ከመከላከያ ሰራዊት ጎን እንደሚቆሙ ከሶማሌ ክልል መገናኛ ብዙሃን ያገኘነዉ መረጃ ያመላክታል ።

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.