Fana: At a Speed of Life!

ከተማ አስተዳደሩ ለመከላከያ ኮምፕሪሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል   ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 28 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለመከላከያ ኮምፕሪሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል 15 ሚሊዮን ብር የሚገመት የሕክምና ቁሳቁስና የአልባሳት ድጋፍ አደረገ።

ድጋፉን ቢሾፍቱ በሚገኘው ሆስፒታል ያስረከቡት የከተማ አስተዳደሩ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ናቸው።

የአገርን ሉዓላዊነት ለማስከበር የተጎዱ ጀግኖችን ማከም ትልቅ ክብር የሚያስገኝ መሆኑ በዚህ ረገድ የሕክምና ድጋፍ እያደረጉ ላሉ ባለሙያዎች ከንቲባዋ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

ለአገር መከላከያ ሰራዊት ድጋፍ እንደ ግዴታ እንጂ እንደ መብት መታየት እንደሌለበትም ገልጸዋል።

በሆስፒታሉ ላለው የሕክምና ባለሙያዎች እጥረት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እገዛ ለማድረግ ሁኔታዎችን እንደሚያመቻች ተናግረዋል።

ከተማ አስተዳደሩ ለመከላከያ ኮምፕሪሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል በዛሬው እለት 15 ሚሊየን ብር ግምት ያለው የህክምና ቁሳቁስና የአልባሳት ድጋፍ ማድረጉን ገልጸው ፥ ድጋፉ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል።

የመከላከያ ኮምፕሪሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል አዛዥ ብርጋዴር ጄኔራል ተገኝ ለታ፥ የከተማ አስተዳደሩ ላደረገው ድጋፍ አመስግነዋል።

ድጋፉ ትልቅ ትርጉም ያለው መሆኑን ጠቅሰው መሰል ድጋፎች የአገር መከላከያ ሰራዊትን የግዳጅ አፈጻጸም እንዲጠናከር አስተዋጽኦ አለው ብለዋል።

ሌሎችም ለመከለከያ ሰራዊት የሚያደርጉትን ሁለንተናዊ ድጋፍ አጠናክረው እንዲቀጥሉ ጥሪ ማቅረባቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

አካባቢዎን ይጠብቁ!

ወደ ግንባር ይዝመቱ!

መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.