Fana: At a Speed of Life!

በጋምቤላ ክልል የአሸባሪዎቹን ቡድን ከማስወገድ ጎን ለጎን ምርትና ምርታማነትን ማሳደግ ይገባል- አቶ ኡሞድ ኡጁሉ

አዲስ አበባ፣ጥቅምት 28፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በጋምቤላ ክልል የአሸባሪዎቹን ቡድን ከማስወገድ ጎን ለጎን የግብርና ልማትን በማጠናከር ምርትና ምርታማነትን ማሳደግ እንደሚገባ የክልሉ ርዕሠ መስተዳድር አቶ ኡሞድ ኡጁሉ ገለፁ።
በክልሉ ርዕሰ መስተዳድርና ምክትል ርዕሰ መስተዳድር የተመራው ቡድን በኢታንግ ልዩ ወረዳ ኢሊያ ቀበሌ የአርሶ አደር ማሳዎችን ጎብኝቷል።
በአዲሱ ምዕራፍ የግብርና ልማትን በማጠናከር በምግብ ሰብል እራስን መቻል በሃገር ደረጃ ልዩ ትኩረት ተሰጥቶት እየተሰራ መሆኑን ርእሰ መስተዳድሩ ተናግረዋል።
ኩታ ገጠም የሆኑ የግብርና ልማቶችን ለመደገፍና ምርትና ምርታማነትን ለመጨመር ከክልል ጀምሮ እስከ ቀበሌ ድረስ ተቀናጅቶ መስራት እንደሚገባም አሳስበዋል።
የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ተንኩዌይ ጆክ÷ አዳዲስ የግብርና ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም የክልሉን አየር ንብረት የተላመዱና ዉጤታማ የሆኑ ሰብሎች ላይ ትኩረት ሰጥቶ መስራት ይገባል ብለዋል።
የኢሊያ ቀበሌ ለሌሎች ተሞክሮ መሆን እንደሚችል፣ ለግብርና ልማት እጅግ ምቹ አካባቢ መሆኑን፣በመንግስት በኩል ተገቢዉ እገዛና ክትትል ከተደረገ ከክልሉ አልፎ ለሃገር የሚተርፍ ምርት ማምረት ይቻላልም ነው ያሉት።
የክልሉ እርሻና ተፈጥሮ ሀብት ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ አጃክ ኡቻላ በበኩላቸው÷ በአርሶ አደሮች የተጠየቁ የትራክተር እና የግብዓት አቅርቦት ችግሮችን ለመፍታት ቢሮው በትኩረት እንደሚሠራ አረጋግጠዋል።
የተፈጥሮ ሃብትን በአግባቡ ማልማት ከተቻለ የክልሉን ብሎም የኢትዮጵያን ምግብ ዋስትና ማረጋገጥ እንደሚቻል ከጋምቤላ ክልል ፕሬስ ሴክረታሪ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
በኢሊያ ቀበሌ 55 ሄክታር ማሳ በክላስተር ማሽላና በለውዝ መሸፈኑን በዚህም 265 አርሶ አደሮች ተጠቃሚ መሆናቸውን የገለጹት÷ የወረዳው እርሻና ተፈጥሮ ሀብት ልማት ቢሮ ቡድን መሪ አቶ ደስታ ዘንገታ ናቸው።
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.