Fana: At a Speed of Life!

የጌዲኦ ዞን አስተዳደር ከዲላ ከተማ አስተዳደር ጋር በመሆን የዘማች ቤተሰቦችን ጎበኙ

አዲስ አበባ፣ጥቅምት 28፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የጌዲኦ ዞን አስተዳደር ከዲላ ከተማ አስተዳደር ጋር በመሆን ዛሬ በዲላ ከተማ የሚገኙ የዘማች ቤተሰቦችን ጎብኝተዋል።
የዘማች ቤተሰቦች ልጆቻቸው ሀገርን ከጠላት ለመከላከልና ኢትዮጵያን ለማዳን የዘመቱ በመሆናቸው የዘማች እናቶችና ቤተሰቦች ሊኮሩ እንደሚገባም ተገልጿል።
ዛሬ በተካሄደው በዚህ ጉብኝት በምክትል አስተዳዳሪ ማዕረግ የጌዲኦ ዞን አስተዳዳሪ አቶ አብዮት ደምሴ ፣ የዲላ ከተማ ከንቲባ አቶ ተስፋጽዮን ዳካ እንዲሁም ሌሎች የዞንና የከተማ አስተዳደሩ የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።
የዞኑ አስተዳዳሪ አቶ አብዮት ደምሴ በዚህ ጊዜ እንደተናገሩት፥ ሀገርን ለማፍረስ የተነሳው ጁንታ ቡድን ለመመከት ልጆቻቸውን መርቀው የላኩት የዲላ እናቶች ክብር ይገባቸዋል የጀግኖች እናቶች በመሆናቸው ሊኮሩ እንደሚገባ ተናግረዋል።
ልጆቻቸው ለኢትዮጵያ ደጀን ለመሆን በመዝመታቸው እናቶቻችውንና ቤተሰባቸውን መንከባከብና መርዳት የኛ ኃላፊነት ነው ስለሆነም በቻለው ሁሉ የዞኑ መንግስት ከከተማ አስተዳዳሩ ጋር በመሆን እንደሚሰራ ጠቁመዋል።
የዲላ ከተማ አስተዳዳር ከንቲባ አቶ ተስፋጽዮን ዳካ በበኩላቸው፥ የሀገራቸውን ጥሪ ተቀብለው ኢትዮጵያን ለማፍረስ ከተነሳው የወንበዴ ቡድን ጋር ለመፋለም የዘመቱ ወጣቶች ጀግኖቻችን ናቸው ቤተሰባቸውን መደገፍ የኛ ድረሻ ነው ብለዋል።
የዘማች ቤተሰቦችን ለመደገፍ በከተማ ደረጃ ኮሚቴ ተዋቅሮ ስራዎች ይሰራሉ ። የቤተሰቦቻቸውን ቤት ማደስ ሰርተው መብላት ለሚችሉት የስራ እድል መፍጠር እና ሌሎች አስፈላጊ ድጋፎች እንደሚደረግላቸውም ተናግረዋል።
የዘማች ቤተሰብ አባላቱም ልጆቻቸው ለኢትዮጵያ በመዝመታቸው ልዩ ክብር እንደሚሰማቸው በመግለጽ በሄዱበት ድል አድርገው እንደሚመለሱም ያለቸውን እምንት ተናግረዋል።
በማስተዋል አሰፋ
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.