Fana: At a Speed of Life!

ከሀረሪ ክልል አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መምሪያ እዝ የተሰጠ መግለጫ

አዲስ አበባ፣ጥቅምት 28፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ከፌደራል የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ዕዝ መምሪያ የሚተላለፉ መመሪያዎች እንደተጠበቁ ሆነው÷ የሀረሪ ክልል አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መምሪያ እዝ በክልሉ ውስጥ ከጥቅምት 29 ቀን 2014 ዓ.ም ጀምሮ ተግባራዊ የሚደረጉ የክልከላ መመሪያዎች አውጥቷል።
ክልከላዎቹም ፦
1. ከፀጥታ አካላት ውጪ ማንኛውም እግረኛ በክልሉ ውስጥ ከምሽቱ 4:00 ሰዓት እስከ ሌሊቱ 11:00 ሰዓት ድረስ መንቀሳቀስ የተከለከለ ነው።
2. ከአምቡላንስ እና ከጸጥታ አካላት ተሽከርካሪ ውጪ ማንኛውም ተሸከርካሪ ከምሽቱ 4፡00 ሰዓት እስከ ሌሊቱ 11:00 ሰዓት ድረስ መንቀሳቀስ የተከለከለ ነው።
በዚህ የጊዜ ገደብ ውስጥ የሚንቀሳቀሱ ከባድ ተሽከርካሪዎችና ሀገር አቋራጭ ተሽከርካሪዎች ከከተማው በስተጀርባ ያለውን መንገድ ወይም ባይ ፓስ መጠቀም ይችላሉ።
3. የክልሉ ሰሌዳ የሌላቸው ማናቸውም ታክሲዎች (ባለ ሶስት እግር ተሽከርካሪናዎች ጨምሮ) ወደ ክልሉ መግባት አይችሉም፤ የክልሉ ሰሌዳ ያላቸው ታክሲዎችም ወደ ሌላ ክልል መውጣት የተከለከለ ነው።
4. ከህክምና ተቋማትና የመድኃኒት ቤቶች በስተቀር ማንኛውም የንግድ ተቋማት ከምሽቱ 4:00 ሰዓት እስከ ሌሊቱ 11:00 ሰዓት አገልግሎት መስጠት አይችሉም።
ጥቅምት 28/2014 ዓ.ም
ሀረር
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
May be an image of text
0
People reached
0
Engagements
Distribution Score
Boost Post
Like

Comment
Share
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.