Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያውያን ፍላጎታቸውን ሊጭኑባቸው ለሚፈልጉ የውስጥና የውጪ ሃይሎች እጅ መስጠት የለባቸውም- ጋዜጠኛ ሄርሜላ አረጋዊ

አዲስ አበባ፣ጥቅምት 28፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ) “ኢትዮጵያውያን የራሳቸውን ፍላጎት ለመጫን ለሚፈልጉ የውስጥና የውጪ ሃይሎች እጅ መስጠት የለባቸውም” ስትል ጋዜጠኛ ሄርሜላ አረጋዊ ገለጸች።
“ስግብግቦችና ተንኮለኞች” የዋህነት እንደድክመት ማየታቸው ስህተት መሆኑን ተናግራለች።
ጋዜጠኛ ሄርሜላ አረጋዊ በትዊተር ገጿ ላይ ባሰፈረችው መልዕክት፥ “ኢትዮጵያውያን ሰብዓዊነትን በማጥፋት የራሳቸውን ከልክ ያለፈ ስግብግብነትና ሀብት ማስጠበቅ ፍላጎታቸው ለሆኑ የውስጥና የውጪ ሃይሎች እጅ መስጠት የለባቸውም” ብለለች።
ዛሬ በአዲስ አበባ በተካሄደው ሰልፍ ላይ የተገኙት ዜጎች በተቀናጀት መልኩ ጥቃት እየተሰነዘረበት ያለውን መሰረታዊ መብታቸውን ለማስከበርና ለመጠበቅ መሆኑን ተናግራለች።
“ስግብግቦችና ተንኮለኞች የዋህነትን እንደ ድክመት እያዩ ሁልጊዜ ይሳሳታሉ” ማለቷን ኢዜአ ዘግቧል።
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.