Fana: At a Speed of Life!

ለመከላከያ ሰራዊት የሚረግ ድጋፍ እንደ ግዴታ እንጂ እንደ ችሮታ መታየት የለበትም- ወ/ሮ አዳነች አቤቤ

አዲስ አበባ፣ጥቅምት 28፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ለመከላከያ ሰራዊት የሚረግ ድጋፍ እንደ ግዴታ እንጂ እንደ ችሮታ መታየት የለበትም ሲሉ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ ገለጹ።
ከንቲባዋ በማህበራዊ የትስስር ገጻቸው ላይ ፥ ዛሬ በቢሾፍቱ የመከላከያ ኮፖርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ዘመናዊ ሆስፒታል ተገኝተን ለኢትዮጵያ ክብርና ሉዓላዊነት አቻ የማይገኝለት ዋጋ የከፈሉ የኢትዮጵያን የቁርጥ ቀን ደራሽ ልጆች ጎብኝተናል ብለዋል።
እንደ ከተማ አስተዳደር 15 ሚሊየን ብር ዋጋ ያላቸዉን የተለያዩ የህክምና የቁሳቁስ ድጋፎችንም አበርክተናል።
በማዕከሉ በጤና ባለሙያነት አገራችሁን በሙያችሁ ጭምር እያገዛችሁ ያላችሁ ባለሙያዎቻችንም ክብር ይገባቹኋል።
በቀጣይም ለተቋሙ የሚያስፈልጉ ማናቸውንም አይነት ድጋፍና ክትትሎች ለማድረግ ወደ ኃላ አንልም ሲሉ ገልጸዋል።
ሁላችንም እነዚህን ጀግኖች በሞራል ጭምር አለንላችሁ ልንላቸው ይገባል።
ሌሎችም ለመከለከያ ሰራዊት የሚያደርጉትን ሁለንተናዊ ድጋፍ አጠናክረው መቀጠል ይገባቸዋል ብለዋል ከንቲባዋ።
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.