Fana: At a Speed of Life!

የሰልጣኞችን የስነ ልቦና ዝግጁነት የሚያጎለብት መርሀ ግብር ተካሄደ

 

 

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 29 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ወጣቶች መከላከያን ለማጠናከር የጀ መሩትን እንቅስቃሴ በከፍተኛ ወኔ መቀጠል እንዳለባቸው የኢትዮጵያ ወታደራዊ አካዳሚ አዛዥ ብርጋዴል ጀነራል ሙሉጌታ አምባቸው አስታወቁ ፡፡

የኢትዮጵያ ወታደራዊ አካዳሚ እና የሜጀር ጀነራል ሙሉጌታ ቡሊ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የሚያሰለጥኗቸውን እጩ መኮንኖችንና ሰልጣኞችን የስነ ልቦና ዝግጁነት የሚያጎለብት መርሀ ግብር ተካሂደዋል ።

ብርጋዴር ጀነራል ሙሉጌታ በመርሃ ግብሩ ላይ እንደተናገሩት፥ እንደ ጀግኖች አባቶቹ ለሰንደቅ ዓላማው ሲል እየተዋደቀ የሚገኘውን ሠራዊታችት ለመምራት መብቃት መቼም ቢሆን የማይገኝ የታሪክ አጋጣሚ መሆኑን አውስተው ፤ እኛም የነሱ ልጆች በመሆናችን ዝናችንን እና ክብራችንን ለማስጠበቅ የምንተጋ እንጂ በተፈጠሩ እና በሚፈጠሩ ሆያሆዬዎች ከጎዞአችን የምንገራገጭ አይደለንም ብለዋል ፡፡

የኢትዮጵያ ወታደራዊ አካዳሚ ለትምህርትና ስልጠና ምክትል አዛዥ ተወካይ ሌተናል ኮለኔል ሸዋቀና አማን እንደነገሩን ፣ እጩ መኮንኖቹና ሰልጣኞቹ በከፍተኛ ሞራል ወደ አካዳሚውና ኮሌጁ ገብተው ስልጠናቸውን በመከታተል ላይ ይገኛሉ ።

መርሀ ግብር ስነ ልቦናዊ ዝግጁነታቸውን እና ተነሳሽነታቸውን ከፍ ለማድረግ ታስቦ የተዘጋጀ ነው ብለዋል ።

የመከላከያ ህዝብ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ኮ/ል ጌትነት አዳነ በበኩላቸው ፣ በህዝብ ጠል ስሪቱ ፣ ሽብርተኛው ቡድን በስርቆት ፣ በማስገደድ እና በግድያ ሱሱ የኢትዮጵያ ስቃይ ሆኖ በመቀጠሉ በተባበረ ክንድ እንደ አንድ ሆነን በመቆም እናስቆመዋለን ብለዋል ፡፡

ቅድሚያ ለእናት ሀገር በሚል የሠራዊታችንን ሞራል በመገንባት ላይ ለሚገኙ የኪነጥበብ ባለሞያዎች ያላቸውን አክብሮት እና ምስጋና አቅርበዋል ፡፡

በዚህ ዝግጅት ላይ ጀነራል መኮንኖች ፣ የኢትዮጵያ ወታደራዊ አካዳሚ እና የሜጀርጀነራል ሙሉጌታ ቡሊ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ አዛዦችና አመራሮች ፣ ከፍተኛ መኮንኖች ፣ የሆለታ ከተማ አመራሮች ፣ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች እና የየአካዳሚዎቹ ማህበረሰብ መሳተፋቸውን የመከላከያ ሰራዊት የፌስቡክ ገጽ መረጃ ያመለክታል።

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.