Fana: At a Speed of Life!

አሸባሪውን ህውሓት በመደምሰስ ሀገራችንን ለማገልገል ወስነናል – የቀድሞ የጦር ሰራዊት አባላት

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 29፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አባላቱ መንግስት ያቀረበውን ጥሪ ተቀብለው ኢትዮጵያ አሁን የገጠማትን ሀገራዊ ፈተና ለመታደግና ወራሪ ሀይሉን በመደምሰስ በሙሉ ፈቃደኝነት ሀገራቸውን ባላቸው ልምድ ለማገልገል መወሰናቸውን ገልጸዋል።
ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት በጎንደር ከተማ ከሚኖሩ የቀድሞ የጦር ሰራዊት አባላት ጋር ቆይታ አድርጓል።
ሻለቃ አለኸኝ ለ14 ዓመት በአዋጊ መኮነንነት ሀገራቸውን ያገለገሉ ሲሆን ÷ በነበረው ስርዓት ተገቢው ክብር እንዳልተሰጣቸውና መደበኛ ህይወታቸውን ለመምራት ይቸገሩ እንደነበር ያስረዳሉ።
እንደ እርሳቸው ገለፃ ብዙ ያልተመለሱላቸው ግለሰባዊ ጥያቄ ቢኖራቸውም ሀገር ችግር ላይ ሁና ይህን ማንሳት ሀገርን ከመካድ እኩል የሚታይ ስለሆነ ያለምንም ማመንታት የመንግሥትን ጥሪ በደስታ መቀበላቸውን ተናግረዋል።
ሀገሬ የእኔ እገዛ የሚያስፈልጋት ሁኖ በተገኘበት ወቅት የትኛውንም መስዋዕትነት ለመክፈል ዝግጁ ነኝ ብለዋል።
የአሁኑ አሸባሪ ቡድን ትናንት በስልጣን በነበረበት ወቅት ለሀገር ክብር የተዋደቁ ጀግኖችን ዋጋ በማሳጣት የቀን ሰራተኝነት ለመስራት የተቸገሩበት ጊዜ መኖሩን የሚያስታውሱት ደግሞ መድፍ ተኳሹ ሻምበል አማረ ናቸው።
ከአማራ ህዝብ ጋር የማወራርደው ሂሳብ አለኝ ያለውን አሸባሪውና ወራሪው ሀይል ተገቢውን እርምጃ በመውሰድ የወለድ ወለድ ሂሳብን ለማወራረድ የእናት ሀገርን ጥሪ ተቀበለው በግንባር በመዝመት ሀገራዊ ግዴታቸውን ለመወጣት በተጠንቀቅ ላይ ናቸው።
ስንጠበቅው የነበረውን ጥሪ በደስታ ተቀብለን የኢትዮጵያን ጠላት ለመፋለምና ጠላቶቿ እንዲጠፉ ለማድረግ አቅማችን በፈቀደው ልክ የሚጠበቅብንን እናደርጋለን ነው ያሉት።
የአሸባሪውን ህውሓት ግፍ ሲያስቡ አብዝተው የሚንዘረዘሩት አስር አለቃ አለማየሁ የ40 ቀን ጨቅላ ልጃቸውን ዐይናቸው እያየ በአሰቃቂ ሁኔታ የገደለ ድርጅት መሆኑን ሲያስቡ እንባ ይተናነቃቸዋል።
ፀረ ኢትዮጵያ እሳቤው ከጥንት አፈጣጠሩ ጀምሮ አብሮ ያደገ ነው የሚሉት ባለታሪካችን አሁን ደግሞ ኢትዮጵያን ከመሰሎቹ ጋር በመሆን ጦርነት መክፈቱን ገልፀው ÷ እኛ የቀድሞ ሰራዊት አባላት ባካበትነው ልምድ እንዋጋዋለን ብለዋል።
ኢትዮጵያ መቼም በየትኛውም መንገድ አሁን የገጠማትን ችግር በልጆቿ ጥረት ተሻግራ በድል ትደምቃለች ብለዋል የቀድሞ የሰራዊት አባላቱ።
በምናለ አየነው
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.