Fana: At a Speed of Life!

ከ44 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመቱ የኮንትሮባንድ እቃዎች ተያዙ

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 29 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ባሳለፍነው ሳምንት ከ 44 ነጥብ 7 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመቱ የገቢና የወጪ የኮንትሮባንድ እቃዎች መያዛቸውን የጉምሩክ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡
ኮሚሽኑ ባደረገው ክትትል ነው÷ ከ 38 ሚሊየን ብር በላይ የገቢ ኮንትሮባንድ እቃዎች እና ከ 6 ነጥብ 7 ሚሊየን ብር በላይ የሚያወጡ የወጪ ኮንትሮባንድ እቃዎቹ የተያዙት፡፡
የገቢ ኮንትሮባንድን በመቆጣጠር ረገድ ቀዳሚውን ስፍራ የሚይዙት አቃቂ ቃሊቲ፣ ድሬድዋ እና ሞያሌ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቶች ሲሆኑ÷ በቅደም ተከተላቸው 13 ነጥብ 3 ሚሊየን፣ 7 ነጥብ 1 ሚሊየን እና 2 ነጥብ 9 ሚሊየን ብር በላይ የሚያወጡ የኮንትሮባንድ እቃዎችን መያዝ ተችሏል፡፡
በቁጥጥር ስር ከዋሉት የኮንትሮባንድ እቃዎች መካከልም አልባሳት፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ መድሀኒት ፣ ጫት፣ አደንዛዥ እጽ፣ የመዋቢያ እቃዎች ፤ የጦር መሳሪያዎችና የተለያዩ ሀገር ገንዘቦች እንደሚገኙበት ከጉምሩክ ኮሚሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.