Fana: At a Speed of Life!

ወ/ሮ አዳነች አቤቤና ፕሮፌሰር ብርሀኑ የ12ኛ ክፍል ፈተና አሰጣጥን ተመለከቱ

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 29 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የ2013 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ከትግራይ በቀር በሁሉም ክልሎች እየተሰጠ ነው፡፡
 
የአዲስ አበባ ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤና የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሀኑ ነጋ በከተማዋ የ12ኛ ክፍል ፈተና አሰጣጥ ሂደትን ተዘዋውረው ተመልክተዋል፡፡
 
አጠቃላይ በሀገር አቀፍ ደረጃ የትግራይ ክልልን ሳይጨምር 617 ሺህ ተማሪዎች የ12ተኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና እየወሰዱ መሆኑ ተመላክቷል፡፡
 
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደርም 36 ሺህ 415 ተማሪዎች ፈተናውን እየወሰዱ መሆኑ ተገልጿል።
 
91 ነጥብ 5 በመቶ የሚሆኑ ተማሪዎች ብሔራዊ ፈተናውን አየወሰዱ መሆኑን የትምህርት ሚኒስትር ፕሮፌሰር ብርሀኑ ነጋ ተናግረዋል፡፡
 
ከንቲባ አዳነች አቤቤ በበኩላቸው በአዲስ አበባ ከተማ ፈተናው በሁሉም የመፈተኛ ጣቢዎች ሰላማዊ በሆነ መልኩ እየተሰጠ መሆኑን ገልጸዋል።
 
በቅድስት ተስፋዬ
 
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.