Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ የኩራታችን ምንጭ በመሆኗ የተጀመረው ትግል ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል- ደስታ ሌዳሞ

 

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 29፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በሀገር ህልውና ላይ የተከፈተብንን ጦርነት በመመከት የሲዳማ ህዝብ የበኩሉን አስተዋጽዖ እንዲያደርግ የሲዳማ ብሔራዊ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ደስታ ሌዳሞ ጠየቁ፡፡

ርዕሰ መስተዳድሩ ይህን ያሉት ዛሬ የሲዳማ ህዝብ አሸባሪዎቹ ህወሀሓት እና ሸኔ እያደረጉ ያለውን ሀገር የማፍረስ ዘመቻን በመቃወም በተጠራው ሰልፍ ላይ ነው።

ህወሓት ላለፉት 27 ዓመታት ሀገራችንን ዘርፏል ፤ ህዝብን ላልተገባ እንግልት እና መከራ ዳርጓልም ነው ያሉት።

ህወሓት የጦር ዐውደ ውጊያውን በአማራ እና አፋር ክልሎች ላይ ቢያደርግም የኢትዮጵያን ህልውና በመፃረር መላውን ህዝባችንን የደፈረ ነው ብለዋል።

የህልውና ዘመቻው የኢትዮጵያ ህዝብን ይበልጥ አንድነቱን የሚያጠናክረው እንጂ የሚያዳክመው አይሆንም ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ ÷ ለዚህም መላው የኢትዮጵያ ህዝብ ጫፍ እስከጫፍ በመነሳት እየመከቱት ይገኛሉ ብለዋል።

ሁለቱ አሸባሪ ኃይሎች የእነሱን ፍላጎት ከሚያራምዱ የውጭ ኃይሎች እና ሚዲያዎች ጋርም በመቀናጀት የሀገራችንን ሉዓላዊነት አደጋ ላይ ጥለዋል ነው ያሉት።

የሲዳማ ህዝብ በተለይ በህወሓት የአገዛዝ ዘመን ይደርስበት የነበረውን ግፍ እና በደል ርዕሰ መስተዳድሩ በንግግራቸው ያስታወሱ ሲሆን ÷ ይህም ታሪክ የማይረሳው ጥቁር ጠባሳ ሆኖ ይዘከራል በማለት አስረድተዋል።

የሲዳማ ህዝብ በለውጡ የተጎናፀፋቸውን አኩሪ ገድሎች ለመቀልበስ ጭምር እየተንቀሳቀሰ ያለውን የህወሓትን ቡድን መላው ህዝባችን ግንባር ድረስ እስከ መዝመት የደረሰ ቁርጠኝነቱን ሊያሳይ ይገባልም ብለዋል።

‘’ኢትዮጵያ የኩራታችን ምንጭ ናት ፤ አረንጓዴ ቢጫ ቀዩ ባንዲራችን የማንነታችን መገለጫ ነው’’ በማለት የተናገሩት አቶ ደስታ ÷ ይህን በአንፀባራቂ መልኩ ለአለም ለማሳየት አሁን የተጀመረው ትግላችን ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል በማለት መናጋራቸውን ከሃዋሳ ከተማ አስተዳደር ህዝብ ግንኙነት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.