Fana: At a Speed of Life!

ኮሚሽኑ በአፋር ክልል በሰው ሰራሽና በተፈጥሮ አደጋ ጉዳት ለደረሰባቸው ዜጎች ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 29 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ)የጉምሩክ ኮሚሽን በሰው ሰራሽ እና በተፈጥሮ አደጋ ጉዳት ለደረሰባቸው ዜጎች እንዲሁም ለአፋር ልዩ ኃይል እና ሚሊሻ አባላት ከ25 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት ቁሳቁሶችን ድጋፍ አድርጓል፡፡

ድጋፉን የተረከቡት የአፋር ክልል ርእሰ መስተዳደር አቶ አወል አርባ ÷የጉምሩክ ኮሚሽን በክልሉ የሰው ሰራሽና የተፈጥሮ አደጋ ባጋጠመ ወቅት ተከታታይ ደጋፎች ማድረጉን ገልጸው በህልውና ዘመቻውም እያደረገ ያለው ሁለንተናዊ ድጋፍ በአፋር ህዝብ ልብ ውስጥ ለዘላለም እንደሚኖር ጠቅሰዋል፡፡

የጉምሩክ ኮሚሽን ኮሚሽር ደበሌ ቀበታ በበኩላቸው ÷አፋር የሠው ልጅ መገኛ ብቻ ሳይሆን በኢትዮጵያነቱ የማይደራደርና ህዝቡንና ድንበሩን የማያስደፍር የጀግኖች መገኛ በመሆኑ ለዚህ ሀገር ወዳድ ህዝብ በችግሩ ጊዜ መቆም እንደሚያስፈልግ መግለፃቸውን ከጉምሩክ ኮሚሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

በድጋፍ ርክክቡ የተገኙት የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ኤርጎጌ ተስፋዬ÷ የሀገር መከላከያ ሰራዊት ጋር በመሆን በአሸባሪው የህዋኃት ቡድን የተቃጣብንን ጦርነት እየመከተ ለሚገኘው ለጀግናው የአፋር ህዝብ እና የአፋር ልዩ ሀይል በተለያየ መንገድ የሚደረገው ሁለንተናዊ ድጋፍ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አስረድተዋል፡፡

አካባቢዎን ይጠብቁ!

ወደ ግንባር ይዝመቱ!

መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.