Fana: At a Speed of Life!

አቶ ሙስጠፌ ሙሁመድ ኡመር በጅግጅጋ የ12ኛ ክፍል ፈተናን አስጀመሩ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 29፣ 2014(ኤፍ ቢ ሲ)የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳደር አቶ ሙስጠፌ ሙሁመድ ኡመር በጅግጅጋ የ12ኛ ክፍል ፈተናን አስጀምረዋል፡፡

የ2013 ዓ.ም 12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ብሄራዊ ፈተና ከጥቅምት 29 እስከ ህዳር 02 ቀን 2014 ዓ.ም ድረስ ይሰጣል።

የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳደርን በፈተና ጣቢያዎች ተገኝተው ፈተናው እየተሰጠ ያለበትን አግባብ ተመልክተዋል ፤ ለተፈታኞችም መልካም ዕድልን ተመኝተዋል።

በሶማሌ ክልል በ2013 ዓ.ም 20ሺህ 211 ተማሪዎች በ128 የፈተና ጣቢያዎች ፈተናውን እንደሚወስዱ የሶማሌ ክልል ትምህርት ቢሮ ሀላፊ አቶ አብዱላሂ አብዲ አደን መግለጻቸውን ከሶማሊ መገናኛ ብዙሃን ኤጀንሲ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.