Fana: At a Speed of Life!

ወጣቶች ህወሓት እስከሚወገድ ለሰራዊቱ ደጀንነታቸውን ሊቀጥሉ ይገባል-የደቡብ ክልል የፖለቲካ ፓርቲዎች

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 29 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በደቡብ ክልል የሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤትወጣቶች የሽብር ቡድኑ ህወሓት ለአንድና ለመጨረሻ ጊዜ እስከሚወገድ ድረስ ደጀንነታቸውን አጠናክረው እንዲቀጥሉ ጥሪ አቅርቧል፡፡
 
በደቡብ ክልል የሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት አባላት በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳይ ላይ ከተወያዩ በኋላ ባለ ሰባት ነጥብ የአቋም መግለጫ በማውጣት ውይይታቸውን አጠናቀዋል ፡፡
 
የአቋም መግለጫው ሙሉ ቃል እንደሚከተለው ቀርቧል፡-
 
1- የህወሀት የሽብር ቡድን እያስከተለ ያለውን ጥፋት የሀገራችን ህዝቦች ለመመከት በዚህ ፈታኝ ወቅት የሚያደርጉትን የትኛውንም ሁኔታ ለመደገፍና የሀገራችንን ህልውና ለመታደግ የበኩላችንን እንደምንወጣ እናረጋግጣለን።
 
2- በአለም አቀፍ ተቋማት በውጭ ሚዲያዎች ና በአንዳንድ የምዕራብ ሀገራት የተዛባና ኢ ፍትሀዊእርምጃ ፍርደ ገምድል በሆነ ውሳኔ የተሳሳተና የተዛባ መረጃ በአገራችን ሉአላዊነትና የግዛት አንድነት የተቃጣብን የተቀናጀ ሴራ አገር የማፍረስ የሸፍጥ ስራ የተለያዩ አካላት አሸባሪውን ለመደገፍ የሚተላለፍ ለአብነት እንደ ቢቢሲ፣ሲኤን ኤን እና ሌሎች የማህበራዊ ሚዲያ አንቂዎች ከዚህ እኩይ ድርጊታቸው እንዲታቀቡ እንዲሁም ተግባራቸውንም አጥብቀን የምናወግዝ መሆናችንን እንገልጻለን።
 
3- የአገራችንም ሆነ የክልላችን ህዝቦች ለመከላከያ ሰራዊታችን ለጸጥታ ሀይሎች ለአገራችን ደጀን በመሆን እየተዋደቁ ለሚገኙ የአገራችን ወጣቶች የሚያደርጉትን የደጀንነት ተግባር እንዲያጠናክሩና የህወሀት የሽብር ቡድን እኩይ ስራ ለአንዴ እና ለመጨረሻ ጊዜ እስከሚወገድ አጠናክረው እንዲቀጥሉ ጥሪ እናቀርባለን ።
 
4- በውጭም በውስጥም ሀይሎች የተቃጣብንን የህልውና አደጋ ለመቀልበስ የአገራችን ህዝቦች በታሪካቸው እንዳሳለፉት በአንድነት እና በትብብር በመቆም የአባቶቻችንን አደራ በመወጣት በታሪክ ፊት በኩራት የምንቆም ህዝቦች እንድንሆን ጠላቶቻችን አገራችንን ለማፍረስ የሚንፈራገጡ ሀይሎችን ቅስም በመስበር ማንኛውንም ጥቃት መመከት እንድንችል አንድ ሆነን ዛሬም ለጠላት የሚፋጅ እሳት ሆነን በጋራ እንድንቆም ጥሪያችንን እናቀርባለን።
5- የክልላችን ህዝቦች በጥፋት ሀይሎች ጥምረትና ተላላኪዎቻቸው በማንኛውም ቀቢጸ ተስፋ ሀይል ሊደረግ የሚችልን የትኛውንም የጸጥታ መደፍረስም ሆነ ሌላ ጥፋት ለመከላከል በየአካባቢው የሰላም ዘብ ሆኖ እንዲቆምና የትኛውንም የኢኮኖሚ ም ሆነ የፖለቲካ አሻጥር እንዲከላከል እናስገነዝባለን ።
 
6- የክልላችን ህዝቦች የህልውና ዘመቻው በአጭር ጊዜ እንዲጠናቀቅና ወደምናልመው የልማትና የአገር ግንባታ ስራችን እንድንመለስ የደጀንነት ስራችንን አጠናክሮ እንዲቀጥልና አገር የመታደግ ሁለንተናዊ የዘመቻ ስራ እንዲያከናውን አበክረን ጥሪ እናቀርባለን።
 
7- መንግስትያወጣው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እና የክተት አዋጅ ለዜጎችን አጠቃላይ ደህንነት በመጠበቅና ዘመቻው ባጠረ ጊዜ እንዲጠናቀቅ በመተግበር ረገድ ጉልህ ሚና ስላለው የፖለቲካ ፓርቲዎች ለአፈጻጸሙ በቁርጠኝነት የምንሰራ መሆናችንን እናረጋግጣለን።
 
ኢትዮጵያ ዛሬም በጸናው የልጆቿ አንድነትና አርበኝነት የተደቀኑባትን አገር የማፍረስ ሴራዎች አልፋ ታፍራና ተከብራ ትኖራለች!
 
የተቃጣብንን ማንኛውን የውጭ እና የውስጥ ባንዳዎች ሴራ ሉአላዊነታችንን የመዳፈር ተግባር በተባበረ ክንዳችን እንመክተዋለን!
 
ጥቅምት 29/2014 ዓ.ም
ሀዋሳ
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.