Fana: At a Speed of Life!

የተባበሩት ዓረብ ኢሚሬቶች ለተፈናቃዮች የሚውል የምግብ እና የተለያዩ ድጋፎችን ላከች

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት29፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የተባበሩት ዓረብ ኢሚሬቶች በኢትዮጵያ ሰብዓዊ እርዳታ ለሚያስፈልጋቸው ዜጎች የሚውል 50 ቶን ምግብን ጨምሮ የተለያዩ የሰብዓዊ ድጋፎችን ልካለች፡፡
በሀገሪቱ ቀይ መስቀል በኩል የተደረገው ድጋፍ 50 ቶን ምግብን ጨምሮ ለጤና አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ ቁሳቁስ ያካተተ ነው ተብሏል፡፡
 
በተጨማሪም በሀገሪቱ በተፈጠረው የጸጥታ ችግር ከመኖሪያ ቀያቸው ለተፈናቀሉ እናቶች እና ህጻናት የሚውል የምግብ እህል መላኩን ኢሚሬትስ የዜና ወኪል ዘግቧል፡፡
 
የተባበሩት ዓረብ ኢሚሬቶች በኢትዮጵያ አስቸኳይ እርዳታ ለሚሹ ወገኖች የምታደርገውን የሰብዓዊ እርዳታ አጠናክር እንድምትቀጥልም በዘገባው ተመላክቷል፡፡
 
አካባቢዎን ይጠብቁ!
 
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
 
መከላከያን ይደግፉ!
 
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.