Fana: At a Speed of Life!

መከላከያ ሰራዊትን በሰው ኃይል ለማጠናከር በሚሰሩ ሥራዎች አመራሩ በትኩረት ሊንቀሳቀስ ይገባል ተባለ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 29፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሀረሪ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ አብዱልጀባር መሀመድ መከላከያ ሰራዊትን በሰው ኃይል ለማጠናከር በሚከናወነው ስራ አመራሩ በትኩረት መንቀሳቀስ ይገባል ሲሉ ተናገሩ፡፡

ሀላፊው ÷ ከወረዳ አመራር ፣ የጸጥታ ኃላፊዎች እና ከሌሎች ጉዳዩ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ውይይት ያደረጉ ሲሆን ÷ ባለፉት ጊዜያት ሀገራዊ ጥሪን በተመለከተ በክልሉ አበረታች ስራዎች መከናወናቸውን ገልጸዋል።

አሸባሪው ህውሓትን ከስር መሰረቱ ለማጥፋት÷ የሀገር መከላከያ ሰራዊትን በሰው ኃይል የማጠናከር ስራ ትኩረት የሚሰጠው በመሆኑ÷ አመራሩ በተደራጀ እና ህዝብን ባሳተፈ መልኩ በመንቀሳቀስ ወጣቱ ሰራዊቱን እንዲቀላቀል ማድረግ ይገባናል ብለዋል።

በተለይ በክልሉ የመከላከያ ሰራዊቱን በሰው ኃይል ከማጠናከር አንጻር ባለፉት ጊዜያት የተከናወኑት አበረታች ስራዎችን በማጎልበት እና ክፍተቶችን በማረም ለተግባራዊነቱ በትኩረት መስራት እንደሚገባ አመላተዋል፡፡

አመራሩ ህዝቡን በማስተባበር የተሰጠውን ሀገራዊ ተልዕኮ በአግባቡ መወጣት ይኖርበታል ያሉት ደግሞ የሀረሪ ክልል የሰላም እና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ሃላፊ አቶ ጥላሁን ዋደራ ናቸው።

በተለይ መከላከያ ሰራዊቱን በሰው ኃይል ለማጠናከር በሚከናወነው ስራ ሁላችንም በኃላፊነት መስራት ይኖርብናል ሲሉም አስገንዝበዋል።

የውይይቱ ተሳታፊዎችም ቀደም ሲል የታዩ ክፍተቶችን በመቅረፍ እና ጠንካራ ስራዎችን በማጎልበት እንዲሁም ቅንጅታዊ አሰራርን በማጠናከር ሰራዊቱን በሰው ኃይል የማጠናከር ስራ እንደሚያከናውኑ መናገራቸውን ከክልሉ መንግስት ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.