Fana: At a Speed of Life!

ሩሲያ 34 የብሪታኒያ የመገናኛ ሳተላይቶችን ወደ ህዋ ላከች

አዲስ አበባ፣ የካቲት 2፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ሩሲያ 34 የብሪታኒያ የመገናኛ ሳተላይቶችን በተሳካ ሁኔታ ወደ ጠፈር መላኳ ተሰምቷል።

ሩሲያ ባለቤትነታቸው “ዋን ዌብ” ለተሰኘ የብሪታንያ ድርጅት የሆኑ 34 የመገናኛ ሳተላይቶችን ወደ ህዋ ማምጠቋን የሀገሪቱ የጠፈር ምርምር ተቋም ሮስኮዝሞስ አስታውቋል።

የመገናኛ ሳተላይቶቹ ሶይዝ በተሰኘ የሩሲያ ሮኬት አማካኝነት በተሳካ ሁኔታ ወደ ጠፈር መላከቸው ተገልጿል።

ተቋሙ ሳተላይቶችን ወደ ህዋ የላከው በፈረንጆቹ 2015 ላይ “ከዋን ዌብ” ኩባንያጋር በነበረው ስምምነት መሰረት ነው ተበሏል።

በቀጣይም “ዋን ዌብ” ከተቋሙ ጋር ባለው ስምምነት መሰረት 600 የሚሆኑ የመገናኛ ሳተላይቶችን ወደ ህዋ የሚልክ መሆኑን ይፋ አድጓል።

በዚህም እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ2021 የተለያዩ መረጃዎችን በዓለም አቀፍ ደረጃ ተደራሽ ለማድረግ ማቀዱ ነው የገለጸው።

ምንጭ ፦ ሽንዋ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.