Fana: At a Speed of Life!

የፋሲል እና የባህር ዳር እግር ኳስ ክለቦች ደጋፊዎች ለተፈናቃዮች 5 ነጥብ 6 ሚሊየን ብር ድጋፍ አደረጉ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 29 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የፋሲል እና ባህር ዳር ከነማ እግር ኳስ ክለቦች ደጋፊዎች ”እኔ አለሁ ለወገኔ” በሚል መሪ ሀሳብ ለተፈናቀሉ ወገኖች ያሰባሰቡትን 5 ነጥብ 6 ሚሊየን ብር ወጪ የተደረገበትን ድጋፍ አስረከቡ።
የድጋፍ አሰባሳቢ ኮሚቴው አባል አቶ ሹመት ጌጡ ከክለቦቹ ደጋፊዎች የተሰበሰበውን ድጋፍ ዛሬ በዘንዘልማ ጊዜያዊ መጠለያ ጣቢያ አስረክበዋል።
የክለቦቹ ደጋፊዎች “እኔ አለሁ ለወገኔ” በሚል መሪ ሃሳብ በአዲስ አበባ ኩፖን በመሸጥና ከባለሃብቶች ድጋፉን መሰባሰባቸውን የኢዜአ ዘገባ ያመለክታል።
ዛሬ የተደረገው ድጋፍ በደብረ ታቦር እና ደባርቅ ግንባሮች ለሚገኙ ተፈናቃዮችም ከነገ ጀምሮ እንደሚቀጥል ነው አቶ ሹመት ጌጡ የገለጹት።
አቶ ሹመት እንዳሉት፥ ክለቦቹ በርካታ ወጣት ደጋፊዎችን የያዙ በመሆናቸው አገራዊና ማህበራዊ ሃላፊነታቸውን ለመወጣት የጀመሩትን ጥረት አጠናክረው ይቀጥላሉ።
ከእዚህም ባሻገር እስከ ግንባር በመዝመት የአሸባሪውን ህወሓት እኩይ ዓላማ በአጭር ጊዜ ውስጥ ለማክሰም በሚደረገው ጥረት የበኩላቸውን እንደሚወጡም አረጋግጠዋል።
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.