Fana: At a Speed of Life!

ከ4 ሚሊየን ብር በላይ በሚገመት የኤሌክትሪክ መሰረተ ልማት ላይ ስርቆት ተፈጽሟል – አገልግሎቱ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 29 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በደቡብ ሪጂን ባለፉት ሦስት ወራት ከ4 ሚሊየን ብር በላይ ግምት ያላቸው የኤሌትሪክ መሰረተ ልማቶች ላይ ስርቆት መፈጸሙ ተገለጸ።
በኤሌክትሪክ መሰረተ ልማቶች ላይ ከጊዜ ወደጊዜ እየተባባሰ የመጣውን የስርቆት ወንጀል ለማስቀረት የሚመለከተው አካል ትኩረት እንዲሰጥም ተጠይቋል።
በአገልግሎቱ የደቡብ ሪጂን የህግ አገልግሎት ሃላፊ አቶ አብዲ ስንታቸው እንደገለጹት፥ በሪጂኑ ባለፉት ሦስት ወራት ብቻ ከ4 ነጥብ 1 ሚሊየን ብር በላይ በሚያወጡ የኤሌክትሪክ መሰረተ ልማቶች ላይ ስርቆት ተፈጽሟል።
የኤሌክትሪክ ሃይል አስተላላፊ ሽቦና ተሸካሚ ምሰሶዎች በዋናነት በከፍተኛ ሁኔታ ስርቆት የሚፈጸምባቸው መሆናቸውንም ተናግረዋል።
“በተለይ በደቡብ ክልል በወላይታ፣ ከምባታና ጠምባሮ ዞኖች እንዲሁም በሲዳማ ክልል አንዳንድ አካባቢዎች የኤሌክትሪክ መሰረተ ልማት ስርቆት ከጊዜ ወደጊዜ እየተስፋፋ መጥቷል” ብለዋል።
ለአብነትም ከቢሻን ጉራቻ እስከ ሃዋሳ አየር ማረፊያ ድረስ የሚዘልቅ ከ20 ኪሎ ሜትር በላይ የተዘረጋ የኤሌክትሪክ ሃይል ተሸካሚ መስመር ተሰርቆ በአሁኑ ወቅት አገልግሎት መቋረጡን ተናግረዋል።
ወንጀሉን ፈጽመዋል በሚል የተጠረጠሩ ከ40 በላይ ግለሰቦች ጉዳያቸው በህግ ሂደት ላይ እንደሚገኝም ነው ሀላፊው የገለጹት።
በመሰረተ ልማቶች ላይ የሚደርሰው ጉዳት የማህበረሰቡን የኤለክትሪክ ሀይል ፍላጎት ከመግታት ባሻገር በሀገር ሀብትና ልማት ላይ እያደረሰ ያለው ጉዳት ከፍተኛ መሆኑንም አስረድተዋል።
በጉምሩክ ኮሚሽን ሃዋሳ ቅርንጫፍ ሻሸማኔ መቆጣጠሪያ ጣቢያ ምክትል ሃላፊ ኢንስፔክተር ተክሌ አጥሮ በበኩላቸው÷ በመስከረም 2014 ዓ.ም 28 ከፍተኛ የኤሌክትሪክ ሃይል አስተላላፊ ጥቅል ሽቦ መያዙን ገልጸዋል።
በወንጀሉ የተጠረጠሩት በሕግ ቀጥጥር ስር እንዲውሉ መደረጋቸውንም ገልጸዋል።
የተያዘው የኤሌክትሪክ እቃ ግምት ከ1 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር በላይ መሆኑንም ኢንስፔክር ተክሌ ተናግረዋል።
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.