Fana: At a Speed of Life!

በሳይበር ደህንነቱ ላይ የተሰነዘሩ በርካታ ጥቃቶችን መመከት መቻሉ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 30፣ 2014(ኤፍ ቢ ሲ) በሳይበር ደህንነቱ የተሰሩ ጠንካራ ስራዎች ኢትዮጵያ ላይ የተሰነዘሩ በርካታ ጥቃቶች መመከት ማስቻሉ ተነገረ።

ሁለተኛው የሳይበር ደህንነት ወር በኢትዮጵያ መጠናቀቁን አስመልክቶ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ÷ ኢትዮጵያ በሶስት ትልልቅ ምክንያቶች ለሳይበር ጥቃቱ ተጋላጭ ሆና ነበር።

መግለጫውን የሰጡት የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ሹመቴ ግዛው ÷ የህዳሴ ግድብ፣ ሃገራዊ ምርጫውና የህግ ማስከበሩ ለጥቃቱ መንስኤ ከሆኑት ዋና ዋናዎቹ ናቸው ብለዋል።

በዚህም በርካታ ጥቃቶች የተሰነዘሩ ቢሆንም እነዚህን ጥቃቶች አስቀድሞ በተሰሩ ስራዎች መመለስ መቻሉን ዳይሬክተሩ ጠቅሰዋል።

በዚህም አደገኛ በተባሉት በእነዚህ ጥቃቶች ሊደርስ የነበረውን ከፍተኛ ኪሳራና ኢኮኖሚያዊ ጫና ማዳን ተችሏል ነው ያሉት።

በርካታ ተከታይና ተጠቃሚ ያላቸው የሳይበር ተጠቃሚዎች በተለይም የመንግስት ተቋማት አስፈላጊውን ዝግጅት፣ ጥንቃቄ እንዲያደርጉና ተቋማቸውን እንዲፈትሹ የማድረግ ስራዎች የተሰራ ሲሆን ÷ ይህም ስኬታማ እንደበር በመግለጫው ተነስቷል።

የሃገር የሳይበር ደህንነቱ የተጠበቀ እንዲሆን ሁሉም ባለድርሻ አካላት የበኩላቸውን ሊወጡ ይገባል ተብሏል።

በሃይማኖት ኢያሱ

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.