Fana: At a Speed of Life!

ወይዘሮ ሙፈሪሃት ካሚል ከዓለም ባንክ የኢትዮጵያ ዳይሬክተር ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 30 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሥራ እና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል ከዓለም ባንክ የኢትዮጵያ ዳይሬክተር ዑስማን ዲዮን ጋር ተወያዩ።

ዳይሬክተሩ ኢትዮጵያ ብዙ ወጣቶች የሚገኙባት አገር እንደመሆኗ መጠን ያላትን ሀብት በመጠቀም እንደ ግብርና እና ቱሪዝም በመሰሉት ዘርፎች ላይ ጠንክራ በመሥራት በክህሎት ብቁ የሆኑ ወጣቶችን ወደ ሥራ ማሰማራት አለባት ብለዋል፡፡

የተለያዩ አገራትን የቴክኒክና ሙያ እንዲሁም የሥራ ተሞክሮ በማንሳት እና በኢትዮጵያ ሥራና ክህሎትን በተመለከተ የሚታዩ ክፍተቶች ላይ ከተወያዩ በኋላ የዓለም ባንክ በቴክኒክና ሞያም ሆነ ሥራን በተመለከተ ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ሚኒስትሯ ሙፈሪሃት በኢትዮጵያ ያሉትን 1 ሺህ 600 ያህል የቴክኒከና ሙያ ተቋማት ብቁ ማድረግ፣ የሥራ ፈጠራ ሃሳብን ከትምህርት ሥርዓት ጋር ማገናኝት፣ ዕውቀትና ቴክኖሎጂን ማሸጋገር ፣ ግብርና እና ቱሪዝምን በመሰሉ እና ብዙ ሰዎችን ሊያካትቱ በሚችሉ የሥራ ዘርፎች ላይ ማተኮር እንዲሁም ኢትዮጵያ ያላትን አቅም ወደ ሥራ መለወጥ የወደፊት አቅጣጫችን ነው ብለዋል፡፡

በኢትዮጵያ የዓለም ባንክ ዳይሬክተር ዑስማን ዲዮን እና ቡድናቸው ቀደም ሲል በኢትዮጵያ ያደረጉትን ሁለንተናዊ ድጋፍ አድንቀው በቀጣይም በጋራ ለመስራት ላሳዩት ተነሳሽነት ምስጋና ማቅረባቸውን ከሥራ እና ክህሎት ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.