Fana: At a Speed of Life!

ለተፈናቃዮች ከ140 ሚሊየን ብር በላይ ድጋፍ ተደረገ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 30፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር ከ140 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ በማድረግ ድጋፍ ማድረጉን አስታወቀ።
ድጋፉ ከ150 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ወገኖች የሚውል መሆኑንም ማህበሩ ገልጿል።
በኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ኃላፊ ዶክተር ሰለሞን አሊ እንዳስታወቁት÷ በግጭቱ ምክንያት የተፈናቀሉ ዜጎች ድጋፍ የሚፈልጉና ትኩረት የሚሹ ናቸው።
ባለፉት ሶስት ወራት ውስጥ የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር በተለያዩ የተፈጥሮና ሰው ሰራሽ ችግሮች ላይ በተለይም በአገሪቱ ከተፈጠሩት ግጭቶች ጋር በተያያዘ በርካታ ሰብአዊ ድጋፎችን ሲያከናውን መቆየቱን አስታውሰዋል።
ማህበሩ በቅርንጫፎቹ አማካኝነት የተለያዩ የሰብአዊ ድጋፍ ለሚሹ ዜጎች ድጋፍ እያደረገ መቆየቱንና ባለፉት ሶስት ወራትም ይህንን ተግባር በማስቀጠል ከቤት ንብረታቸው ለተፈናቀሉ ዜጎች በርካታ የድጋፍ አገልግሎት ማከናወኑን ኢፕድ ዘግቧል።
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
May be an image of 1 person
0
People reached
4
Engagements
Distribution score
Boost post
4
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.