Fana: At a Speed of Life!

ከተማ አስተዳዳሩ ወሎ ግንባር ለሚገኘው የመከላከያ ሰራዊት ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 30 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳዳር ወሎ ግንባር ለሚገኙ የመከላከያ ሰራዊት አባላት ከ20 ሚሊየን ብር በላይ የሚያወጣ የአይነት ድጋፍ አድርጓል፡፡
 
ድጋፉን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ ወሎ ግንባር በመገኘት ለመከላከያ ሰራዊት አስረክበዋል፡፡
 
የተደረገው የአይነት ድጋፍም 100 ሰንጋዎችን ጨምሮ 20 ሚሊየን ብር በላይ የሚያወጣ የዕለት ምግብ መሆኑ ነው የተገለጸው፡፡
 
ወይዘሮ አዳነች አበቤ እናንተ ለኢትዮጵያ ስትሉ ህይወታችሁን እየሰጣችሁ እና የኢትዮጵያን አንድነት ለመጠበቅ ኢትዮጵያ ቀና እንድትል እየተፋለማችሁ ነው ውለታችሁ አለብን ብለዋል፡፡
 
ሀገር ለማፍረስ የመጣውን የሽብር ቡድን ለመፋለም ብቻችሁን አይደላችሁም፤ ገንዘብ ብቻም አይደለም ህይወት ለመስጠት ዝግጁ ነን ብለዋል ከንቲባ አዳነች አቤቤ።
 
ዛሬ ይዘን የመጣነው ድጋፍ አብረናችሁ ነንለማለት ነው ያሉት ከንቲባዋ÷ በቀጣይም ለሰራዊቱ ቤተሰብ ድጋፍ እንደሚደረግ አረጋግጠዋል፡፡
 
የወሎ ግንባር ኮማንድ ፖስት ድጋፍ ሰጪ ቡድን አስተባባሪ ተወካይ ሜጄር ጄነራል ሀብታሙ ጥላሁን በበኩላቸው÷መከላከያ አሸናፊ የሚሆነው የህዝብ ደጀንነቱ ተጠናክሮ ሲቀጥል መሆኑን አንስተዋል፡፡
 
እስካሁን ሰራዊቱ ከህዝብ ከፍተኛ ድጋፍ አልተለየውም፤ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳድር ድጋፍም ሰራዊቱን ይበልጥ እንደሚያበረታታው አውስተዋል፡፡
 
ሀገር ለማፍረስ እያሴሩ ያሉትን የሽብር ቡድኖችም በአጭር ጊዜ ቀብረን ድል እናበስራለን ነው ያሉት፡፡
 
በብስራት መንግስቱ እና አላዩ ገረመው
 
አካባቢዎን ይጠብቁ!
 
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
 
መከላከያን ይደግፉ!
 
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.