Fana: At a Speed of Life!

በጌዴኦ ዞን አሸባሪው ህወሓትና ሸኔን የሚያወግዝ ሰልፍ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 30፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ)በጌዴኦ ዞን በይርጋጨፌ ወረዳና በይርጋጨፌ ከተማ አሸባሪው ህወሓትና ሸኔን የሚያወግዝ ሰልፍ እየተካሄደ ነው።
ሰልፉ አሸባሪው ቡድን የከፈተውን የክህደት ጦርነት ለመመከትና ከመከላከያና መንግሥት ጎን ለመቆምና የተደረገ ነው።
በህዝባዊ ሰልፉ ህወሓትና ሸኔ ኢትዮጵያን ለማፍረሰ የሚያደርጉትን እኩይ ድርጊት ተወግዟል ። በሺዎች የሚቆጠሩ የይረጋጨፌ ወረዳና የይርጋጨፌ ከተማ ነዋሪዎች ተሳትፈዋል።
ህዝቡ በሰልፉ ላይ ለቀረበልን የክተት ጥሪ በህዝባዊ ቁጭትና ፅናት ተሰልፈናል ፣ የአሸባሪውን የህወሓት ቀቢፀ -ተስፋ በትግላችን እናመክናለን፣ በእኛ መስዋዕትነት ኢትዮጵያ ታፍራና ተከብራ ትኖራለች አካባባየን እጠብቃለሁ ኢትዮጵያን ለማዳን እዘምታለሁ እኔ ሠራዊት ነኝ ከመከላከያ ጎን እሰለፋለሁ ፣ ሀገር ለማፍረሰ የተቃጣውን ጦርነት አጥብቄ እቃወማለሁ ፣ በሰሜን እዝ መከላከያ ሠራዊት ላይ የተደረገውን ጭፍጨፋ አልረሳውም የሚሉና ሌሎች መፈክሮችን አስተጋብቷል።
የሰልፉ ተሳታፊዎች ከመንግስትና ከመከላከያ ጎን በመሆን ጦርነቱን ለመመከት አስፈላጊውን ሁሉ ለማድረግ መዘጋጀታቸውን ተናግረዋል።
አሸባሪው ቡድን ጠፍቶ ኢትዮጵያ ሠላሟ እስኪረጋገጥ ድረስ ትግላችንን እንቀጥላለን ፣ መቼም የህወሓት ኢትዮጵያን የማፍረስ ህልም እኛ እያለን እውን አይሆንም በኛ ደምና አጥንት ኢትዮጵያ ትቀጥላለች ብለዋል።
ጀግናው የሀገር መከላከያ ሠራዊት በየግንባሩ እየተቀዳጀ ያለው ድል ያኮራናል ምንግዜም የምናደርገውን ድጋፍና ህዝባዊ ደጀንነታችን አጠናከረን እንቀጥላለን ብለዋል።
ኢትዮጵያ እያደረገች ያለችው የእውነትና የፍትህ ጦርነት በድል ይጠነቀቃል ነው ያሉት።
በማስተዋል አሰፋ
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
19
2 Shares
Like

 

Comment
Share
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.