Fana: At a Speed of Life!

በመዲናዋ የጦር መሳሪያ ምዝገባ እስከ ህዳር 3 ቀን እንዲቀጥል ተወሰነ

አዲስ አበባ፣ጥቅምት 30፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የጦር መሳሪያ ምዝገባው እስከ ህዳር 3 ቀን 2014 ዓ.ም ይቀጥላል ሲል የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ፡፡
የጦር መሳሪያ በእጁ የሚገኝ ማንኛውም ግለሰብ ፈቃድ ያለውም ሆነ የሌለው የመዲናዋ ነዋሪ በሁሉም ክፍለ ከተሞች እና በስሩ በሚገኙ ፖሊስ ጣቢያዎች እየቀረበ መሳሪያውን እንዲያስመዘግብ ጥሪ መቅረቡ ይታወሳል፡፡
ጥቅምት 23 ቀን 2014 ዓ.ም በተሰጠው መመሪያ የጦር መሳሪያ ያላቸው ግለሰቦች በተራዘመው የጊዜ ገደብ መሰረት እስከ ጥቅምት 27 ቀን 2014 ዓ.ም ድረስ እየቀረቡ ሲያስመዘግቡ መቆየታቸውንም ፖሊስ አስታውቋል፡፡
ምዝገባውን በሃገር አቀፍ ደረጃ ወጥ ለማድረግ መታሰቡን እና አሁንም በተለያዩ ምክንያቶች ያላስመዘገቡ ግለሰቦች ባቀረቡት ጥያቄ መሰረት እስከ አርብ ህዳር 3 ቀን 2014 ዓ.ም እንዲቀጥል የተወሰነ በመሆኑን ገልጿል፡፡
የጦር መሳሪያ ያላስመዘገቡ የመዲናዋ ነዋሪዎች የጊዜ ገደቡ ከመጠናቀቁ በፊት በአቅራቢያችሁ በሚገኙ ፖሊስ ጣቢያዎች እየቀረባችሁ እንድታስመዘግቡ ሲል ጥሪ ማቅረቡን ከአዲስ አበባ ፖሊስ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
No photo description available.
0
People reached
3
Engagements
Distribution score
Boost post
3
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.