Fana: At a Speed of Life!

”በቴክኖሎጂ ውንብድና እና በማኅበራዊ ሚዲያ ሽብር ኢትዮጵያን ማሸነፍ አይቻልም’- ዶ/ር ሹመቴ ግዛው

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 30 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ”በቴክኖሎጂ ውንብድና እና በማኅበራዊ ሚዲያ ሽብር ኢትዮጵያን ማሸነፍ አይቻልም” ሲሉ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ ዋዳ ዳይሬክተር ዶክተር ሹመቴ ግዛው ተናገሩ።
 
ኤጀንሲው የተለያዩ ተግባራት የተከወኑበትን አገር አቀፍ የሳይበር ደህንነት ወር መጠናቀቅ አስመልክቶ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቷል።
 
የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ሹመቴ ግዛው፤ ከኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ ጋር ተያይዞ የማኅበራዊ ሚዲያ ባለቤቶችና ዋናዋና የምዕራባዊያን መገናኛ ብዙሃን አሉታዊ ተጽዕኖ የመፍጠር ዘመቻ እያካሄዱባት መሆኑን አንስተዋል።
 
የማኅበራዊ ሚዲያ ባለቤቶች ሆን ብለው ኢትዮጵያንና ወዳጆቿን ለማሸበርና ለማጥቃት እየሰሩ መሆኑን ጠቅሰው “ኢትዮጵያ ትልቅ አገር ናት፤ ሕዝቦቿም ታላቅ ናቸው ይህ የማይሳካ ነው” ብለዋል።
 
በቴክኖሎጂ ውንብድና እና በማኅበራዊ ሚዲያ ሽብር ኢትዮጵያን ማሸነፍ እንደማይቻልም ነው ዶክተር ሹመቴ የተናገሩት።
 
“እንደ አገር ራሳችንን የቻልን ነን ካልን በቴክኖሎጂውም ራሳችንን ችለን ማሳየት አለብን” ያሉት ዶክተር ሹመቴ ይህን እውን ለማድረግ አማራጭ የማኅበራዊ ሚዲያ መተግበሪያዎችን የማልማት ስራ እየተከናወነ እንደሆነ የኢዜአ ዘገባ ያመለክታል።
 
ዶክተር ሹመቴ አገር አቀፍ የሳይበር ደህንነት ወር በተለያዩ ተቋማት መጠነ ሰፊ የሳይበር ደህንነት ግንዛቤ በመፍጠር መጠናቀቁን በመግለጫቸው ጠቁመዋል።
 
ከመቼውም ጊዜ በላይ የሳይበር ምህዳር ተጠቃሚውን ማኅበረሰብ ተደራሽ ለማድረግ ውጤታማ ስራ መሰራቱንም አንስተዋል።
 
በተለይም ቁልፍ ለሚባሉ የመንግስት ተቋማት በሳይበር ደህንነት ላይ ስልጠናዎችና የግንዛቤ ማስጨበጫ ተግባራት መከወናቸውንም ገልጸዋል።
 
አካባቢዎን ይጠብቁ!
 
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
 
መከላከያን ይደግፉ!
 
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.