Fana: At a Speed of Life!

የሀገር ሉአላዊነትን አሳልፈው የሸጡ ባንዳዎች በታሪክ ብቻ ሳይሆን ዛሬም አሉ – ምሁራን

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 30 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ለራሳቸዉ ጥቅም ሲሉ የሀገር ሉአላዊነትና የወገንን ነጻነት አሳልፈው የሸጡ ባንዳዎች በታሪክም ነበሩ፥ ዛሬም ክህደታቸውን እየፈጸሙ ነውሲሉ የጅማ ዩኒቨርሲቲ ምሁራን ገለፁ።
በጅማ ዩኒቨርሲቲ የሚዲያና ኮሚዩኒኬሽን መምህር ዶክተር ደመላሽ መንግስቱ ፥ “ህወሓት ከስልጣን ለሚያገኘው ጥቅም ሲል ሀገርን ከድቷል፤ ህዝብን ለጦርነት ዳርጓል” ብለዋል።
አሸባሪው ህወሓት ለጥቅሙ ሲል የውጭ ሀገራት ተልእኮዎችን ለማስፈጸም ሌት ተቀን እየዳከረ መሆኑ፣ ለሀገሩና ለወገኑ ቅንጣት ታክል የሚያስብ ህሊና ያልፈጠረበት ከሀዲ መሆኑን ማሳያ ነው” ሲሉ ገልጸውታል።
“ባለፉት አመታት እንዳየነው ቡድኑ የሴራ መረቡን መዘርጋት የጀመረው በሀሳብ የተለዩ ዜጎችና የገዛ ወገኖቹን ጭምር በመግደልና በማጥፋት ነበር ” ሲሉ አስታውሰዋል።
ህወሓት በስልጣን በነበረበት ባለፉት 27 አመታት ያልፈጸመው ወንጀል፣ ያልዘረፈው የሀገር ሀብት እንዳልነበር የገለጹት ዶክተር ደመላሽ ፥ ዛሬም ከስልጣን ተወግዶ የጥፋት ባህርይውን በግልጽና በአደባባይ ንፁሃንን እየረሸነ መሆኑን ተናግረዋል።
ህዝቡ በማህበራዊ መገናኛ ዘዴዎች በሚለቀቁ በአሸባሪው የሀሰት ፕሮፓጋንዳዎች ሳይታለል አንድነቱን ጠብቆ በተደራጀ አግባብ በመታገል የከሀዲዎችን ሴራ መቀልበስ ይጠበቅበታል” ሲሉ መክረዋል።
የጅማ ዩኒቨርሲቲ የታሪክ መምህር ረዳት ፕሮፌሰር ታሪኩ ለሜሳ በበኩላቸው፥ “በዓለም ላይ በየትኛውም ሀገር መንግስት ሆኖ ያስተዳደረ አካል የሕወሓትን ያህል ክህደት የፈጸመ በታሪክ የለም” ብለዋል።
ጨካኙ የሀገር ከሀዲ ህወሓት በማይካድራ፣ በአፋርና በወሎ ንጹሀንን በጅምላ በመጨፍጨፍ የፈጸመው ወንጀል የአጥፍቶ ጠፊነት ባህሪውን ያሳየ መሆኑን አመልክተዋል።
“ቡድኑ ጭካኔውን በንጹኋን እናቶች፣ ሴቶችና ህጻናት ላይ ማሳየቱ ሀገርን በማፍረስና በማዳከም ለውጭ ጠላት አሳልፎ የመስጠት የክህደት ግብሩን ለመፈጸም የሚያደርገው ጥረት ነው” ሲሉ ረዳት ፕሮፌሰር ታሪኩ ተናግረዋል።
ኢትዮጵያዊ አንደነትንና የትግል አቅምን በማጠናከር የባንዳነትና የክህደት ባህሪ የማይለቀውን ህወሀትን እስከመጨረሻው ማስወገድ እንደሚገባ መናገራቸውን ኢዜአ ዘግቧል።
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
0
People reached
1
Engagement
Boost post
1
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.