Fana: At a Speed of Life!

አምነስቲ ኢንተርናሽናል ይፋ ያወጣው የሽብርተኛው የህወሓት አረመኔያዊ ድርጊት በሰው ዘር ሁሉ ሊወገዝ ይገባል- የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት

 

አዲስ አበባ፣ ህዳር 01 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አምነስቲ ኢንተርናሽናል ይፋ ያወጣው የሽብርተኛው የህወሓት አረመኔያዊ ድርጊት የሰው ዘር ሁሉ ሊያወግዘው የሚገባ መሆኑን የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት አስታወቀ።

ለሰው ዘር ሕይወት ጠላት የሆነው የህወሓት የሽብር ቡድን ከዚህ በላይ ወንጀል እንዳይፈጽም አንድ ሆነን ከዚህ አረመኔያዊ ድርጊቱ ልናስቆመው፣ ዓለምም ሊያወግዘው ይገባል ብሏል።

የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ዛሬ ባወጣው መግለጫ፥ የሽብር ቡድኑ ህወሓት በወረራ በያዛቸው አካባቢዎች ላይ እየፈጸመ ስለሚገኘው አሰቃቂ የሰብአዊ መብት ጥሰቶች መንግሥት በተለያየ መልኩ ሲያሳውቅ መቆየቱን አስታውሷል።

የአሁኑ የአምነስቲ ኢንተርናሽናል ሪፖርትም የሽብር ቡድኑ እያደረሰ ያለው የሰብአዊ መብት ጥሰት የባህሪው መገለጫ መሆኑን  ያጋለጠ ነው ብሏል።

አምነስቲ ኢንተርናሽናል፥ አሸባሪው የህወሓት ቡድን በወረራ በያዛቸው የአማራ ክልል አካባቢዎች ላይ ከፍተኛ የሰብአዊ መብት ጥሰቶችን ሲፈጽም መቆየቱን የጥቃቱ ሰለባ የሆኑ ሴቶችን አነጋግሮ ያጠናቀረውን ሪፖርት ይፋ ማድረጉን አስመልክቶ ነው የኮሙኒኬሽን አገልግሎት ይህን መግለጫ ያወጣው።

በአማራ ክልል በተለይ ነፋስ መውጫ አካባቢ በሚኖሩ 16 ሴቶች ላይ የህወሓት የሽብር ቡድን አባላት ሰው የሆነ ፍጡር ሊፈጽመው ቀርቶ ሊያስበው የሚይገባውን በቡድን አስገድዶ የመድፈር ወንጀል እንደፈጸሙባቸው ተጎጂዎቹ ለአምነስቲ ኢንተርናሽናል ተናግረዋል።

ለአምነስቲ ኢንተርናሽናል ምስክርነታቸውን የሰጡት ተጎጂዎች እንደተናገሩት፥ የአሸባሪው ቡድን ሕወሐት ታጣቂዎች በመሣሪያ በማስፈራራት በአሰቃቂ ሁኔታ በቡድን አስገድዶ የመድፈር ወንጀል ተፈጽሞባቸዋል፤ ቤት ንብረታቸው ተዘርፏል።

ሕጻናት ልጆቻቸው ጭምር አሰቃቂውን ተግባር በዓይናቸው እንዲያዩና የዘለዓለም ቁስል እንዲፈጠርባቸው ተደርጓል።

የሕክምና ጣቢያን ጨምሮ የተለያዩ አገልገሎት መስጫ ተቋማትን የሽብር ቡድኑ አባላት እንዳቃጠሉም ሪፖርቱ አረጋግጧል።

አምነስቲ ኢንተርናሸናል እንደገለጸው፥ ነፋስ መውጫን ለዘጠኝ ቀናት በወረራ ይዞ የቆየው አሸባሪ ቡድን በእነዚህ ቀናት ውስጥ ከ70 በላይ ሴቶችን አስገድዶ ደፍሯል።

ይሄንንም ሀቅ የጥቃት ሰለባዎቹ ለክልሉ የሥራ ኃላፊዎች ማሳወቃቸውን አምነስቲ ኢንተርናሸናል አረጋግጧል።

የማይካድራ ጭፍጨፋ ሲፈጸም ዓለም ይሄንን የሽብር ቡድን ቢያስቆመው ኑሮ፣ በዚህ ሪፖርት የተገለጡትና ያልተገለጡት የሰው ልጅ ሰቆቃዎች ባልቀጠሉ ነበር ብሏል የኮሙኒኬሽን አገልግሎት በመግለጫው።

አሸባሪው ሕወሐት በተለያዩ አካባቢዎች በሰው ዘር ላይ ሊፈጸሙ የማይገባቸውን ወንጀሎች መፈጸሙን ገልጾ፥ ይሄንንም የተለያዩ ተቋማት ቢዘገይም እየገለጡት ነው ብሏል።

የአምነስቲ ሪፖርት የተጠናቀረው የሽብር ቡድኑ ተሸንፎ በለቀቃቸው አካባቢዎች መሆኑን የገለጸው የኮሙኒኬሽን

አገልግሎት፤ አሁንም በወረራ በያዛቸው አካባቢዎች ከዚህ የባሰ ኢሰብአዊ ድርጊት እየፈጸመ እንደሚገኝ አስታውቋል።

የሰብአዊ መብት ተቋማት ምርመራቸውን አስፍተው ይሄንን ዘግናኝ ተግባር ለዓለም እንዲያሳውቁ ኃላፊነት እንዳለባቸውም አሳስቧል።

ይህ ለሰው ዘር ሕይወት ጠላት የሆነ የሽብር ቡድን ከዚህ በላይ ወንጀል እንዳይፈጽም የኢትዮጵያ ሕዝብ አንድ ሆኖ ሊያስቆመው፣ ዓለምም ሊያወግዘው ይገባል ሲልም የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት አስገንዝቧል።

አካባቢዎን ይጠብቁ!

ወደ ግንባር ይዝመቱ!

መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.