Fana: At a Speed of Life!

የሽብር ቡድኑን ተልዕኮ ፈጻሚ የተባሉ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 01፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ትግበራ በአዲስ አበባ የሽብር ቡድኑ ህውሓትን ተልዕኮ ለማስፈፀም ሲንቀሳቀሱ ነበር የተባሉ  ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡

የፌደራል ፖሊስ የወንጀል መከላከል ዘርፍ ሃላፊ ምክትል ኮሚሽነር ጀነራል መላኩ ፈንታና የአዲስ አበባ ፓሊስ ኮሚሽነር ጌቱ አርጋው  በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ መሰረት በወንጀል መከላከልና ምርመራ ረገድ በተሰሩ ተግባራትና  በተካሄደው ኦፕሬሽን ዙሪያ መግለጫን እየሰጡ ነው።

በመግለጫቸውም በፍተሻና በብርበራ የተገኙ ውጤቶችን ጨምሮ ፖሊስ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ መሠረት የማስፈጸሚያ አደረጃጀት በመፍጠር አባላቱ አዋጁን በሚገባ እንዲያውቁት ከማድረግ ጀምሮ ሕዝብና ፖሊስን አስተባብሮ ሥራውን እያከናወነ ይገኛል ብለዋል።

ከተራ ሌብነት ጀምሮ ዜጎችን እየገደለና እያሰቃየ የሚገኘዉ የሽብር ቡድኑ ህወሓት አላማውን ለማስፈፀም የሚረዱት እንደ  ሸኔ፣ ቅማንትና  የጉምዝ ታጣቂዎችን አስተባብሮ ሽብሩን ወደመሃል ሀገር ለመሳብና አዲስ አበባ ዙሪያ ለማድረግ እየሰራ ነውም ብለዋል።

ለዚህም በከተሞች ውስጥ ተመሳስሎ በመግባት ሙከራ እያደረገ ነው ያሉት ጀነራሉ እንቅስቃሴዉን ለመግታት የተለያዩ የፀጥታ አካላት  የአዲስ አበባ ፖሊስ፣ የኦሮሚያ ፖሊስ፣ ሪፐብሊካን ጋርድ እና የደህንነት መስሪያቤቱን ጨምሮ እየሰሩ ነው ብለዋል።

በዚህም የሽብር ተልዕኮውን ማስፈፀሚያ የሆኑ የሀገር ውስጥና የውጭ ገንዘቦች፣ አሳሳች መረጃዎች የተለያዩ የፀጥታ አስከባሪ አባላት አልባሳትን ሲያሰፉ እና ሲያዘጋጁ በቁጥጥር ስር ውሏል ብለዋል።

ከዚህ ውስጥም የትግራይ ክልል ልዩ ሃይል፣ የአፋር ክልል ልዩ ሃይል፣ የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ እና የማረሚያ ቤት ደንብ ልብሶችን ጨምሮ ወታደራዊ ማዕረጎች በሀሰት ሲዘጋጁ በቁጥጥር ስር ውለዋል ነው ያሉት።

በሌላ በኩል የጎዳና ተዳዳሪ በመምሰል ብዙ ጥሬ ገንዘብ የያዙ ከአንድም ሁለት ባንክ አካውንት ያላቸው፣ የኔቢጤ በመምሰል የስለላ ስራን የሚሰሩ፣ ሆቴሎች፣ ፔንሲዮኖችና አደንዛዥ እፅ በሚያስጠቅሙ ቤቶች ቀን  የሚደበቁና በምሽት የሽብር ቡድኑን ህወሓት ተልዕኮ ለማስፈፀም ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ተጠርጠሪዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተገልጿል፡፡

በፀጋዬ ወንድወሰን

 

አካባቢዎን ይጠብቁ!

ወደ ግንባር ይዝመቱ!

መከላከያን ይደግፉ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.