Fana: At a Speed of Life!

በክልሉ ከህወሓትና ሸኔ ጋር ግነኙነት አላቸው የተባሉ ከ300 በላይ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ዋሉ 

አዲስ አበባ፣ ህዳር 01፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በሀረሪ ክልል ከአሸባሪው ህወሓትና ሸኔ ጋር ግነኙነት አላቸው ተብለው የተጠረጠሩና የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን መመሪያ የተላለፉ ከ300 በላይ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የክልሉ ጠቅላይ ዓቃቤ ህግ አስታወቀ።

የክልሉ ጠቅላይ ዓቃቤ ህግ ዋና ዓቃቤ ህግ አቶ አዩብ አህመድ  እንደገለጹት÷በክልሉ አስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ለማስከበር የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መመሪያ እዝ ወጥቶ የተለያዩ ስራዎች እየተከናወኑ ነው፡፡

በዚህም በክልሉ ከአሸባሪዎች ህወሓትና ሸኔ ጋር ግነኙነት አላቸው ተብለው የተጠረጠሩ እና የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን የጣሱ  ከ300 በላይ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ተናግረዋል።

ከተጠርጣሪዎቹ ግለሰቦች ላይ የጦር መሳሪያ ፣ የተለያዩ ተንቀሳቃሽ እና ተንቀሳቃሽ ያልሆኑ ንብረቶች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ነው አቶ አዩብ የተናገሩት።

በክልሉ ከአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ አፈጻጸም እና ክልከላ ጋር በተገናኘ ተጠርጣሪዎችን አጣርቶ ለህግ የሚያቀርብ በዓቃቤ ህግ እና መርማሪ ፖሊሶች የሚመራ የምርመራ ቡድን መዋቀሩን ጠቁመው÷ በዚህም ነጻ የሆኑ ግለሰቦች እንደሚለቀቁ ተናግረዋል።

እንደ አቶ አዩብ ገለጻ ከአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ አፈጻጸም እና ክልከላ ጋር በተገናኘ ተግባራዊ ያላደረጉ ግለሰቦች ላይ ክስ እንደሚመሰረትም አብራርተዋል።

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ አፈጻጸም ግቡን እንዲመታ እና በአጭር ጊዜ አላማውን እንዲያሳካ ህብረተሰቡ ከጸጥታ አካላት ጎን በመሆን እየሰጠ ያለውን ድጋፍ አጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ ማቅረባቸውን ከክልሉ ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

 

አካባቢዎን ይጠብቁ!

ወደ ግንባር ይዝመቱ!

መከላከያን ይደግፉ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.