Fana: At a Speed of Life!

ሴት የመንግስት ሰራተኞች ለመከላከያ ሰራዊት ስንቅ እያዘጋጁ ነው

 

አዲስ አበባ፣ ህዳር 2፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በደቡብ ክልል ሴት የመንግስት ሰራተኞች ለሀገር መከላከያ ሰራዊትና ለጸጥታ አካላት የሚሆን ስንቅ በማዘጋጀት ላይ ናቸው፡፡

 

በስንቅ ዝግጅቱ  ከሁሉም መስሪያ ቤቶች የተውጣጡ ሴት የመንግስት ሰራተኞችና ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች የተሳተፉ ሲሆን÷ ለመከላከያ ሰራዊቱና ለጸጥታ ኃይሉ ደጀንነታቸውን ለመግለጽ  ያለመ ነው።

 

በክልሉ 17 ሚሊየን ብር ግምት ያለው ስንቅ ለማዘጋጀት መታቀዱን የደቡብ ክልል ሴቶችና ህጻናት ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ባይዳ ሙንዲኖ ገልጸዋል፡፡

 

በክልሉ የሚገኙ ሴቶችን በማሳተፍ የሀገርን ህልውና ለማስጠበቅ እየተዋደቀ ላለው ለሀገር መከላከያ ሰራዊትና የጸጥታ ኃይል የስንቅ ድጋፍ ይደረጋልም ነው ያሉት፡፡

 

በስንቅ ዝግጅቱ እየተሳተፉ የሚገኙ ሴት የመንግስት ሰራተኞች በበኩላቸው÷ ሀገርን ከወራሪ ለመታደግ እየተፋለመ ላለው ሰራዊት የሚያስፈልገውን ስንቅ ማዘጋጀት ከእኛ ይጠበቃል ብለዋል።

 

ልጆቻችንን መርቀን ወደ ግንባር ከመሸኘት በተጨማሪ ሰራዊቱን በስንቅ እና ተዛማጅ ጉዳዮች መደገፍ ይገባል ማለታቸውን ከደቡብ ክልል ኮኮሙኒኬሽን  ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.