Fana: At a Speed of Life!

የመዲናዋ ወጣቶች ተደራጅተው ከተማቸውን እየጠበቁ ነው

አዲስ አበባ፣ ህዳር 2፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ ከ27 ሺህ በላይ ወጣቶች ተደራጅተው የከተማቸውን እና የአካባቢያቸውን ሰላም እና ፀጥታ በመጠበቅ ላይ መሆናቸው ተገለጸ፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ኃላፊ አቶ አብርሃም ታደሰ በከተማዋ የጸረ ሰላም አካላትን እንቅስቃሴ ለመቆጣጠር ከ27 ሺህ በላይ ወጣቶች ከጸጥታ አካላት ጋር ተቀናጅተው አጠቃላይ የከተማዋን እና የአካባቢያቸውን ሰላም በመጠበቅ ላይ እንደሚገኙ አስታውቀዋል።
አሸባሪው ሕወሓት በኢትዮጵያ ላይ በከፈተው ግልጽ ጦርነት ምክንያት ሰፊ የህዝብ ተሳትፎና አንድነት እየታየ መሆኑን የገለጹት አቶ አብርሃም በዚህ ወቅት የወጣቱ ሚና የጎላ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡
ወጣቶቹ “እኔ የከተማዬ የሠላም ዘብ ነኝ ” በሚል መሪ አካባቢያቸውን ከመጠበቅ ባለፈ የመከላከያ ሠራዊቱን በመቀላቀልና ለሠራዊቱ ደጀን በመሆን በቁርጠኝነት እየተንቀሳቀሱ ነው ማለታቸውን ከአዲስ አበባ ፕሬስ ሴክሬታሪያት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.