Fana: At a Speed of Life!

በኦሮሚያ ክልል ለ2 ነጥብ 6 ሚሊየን ነዋሪዎች የኮቪድ 19 ክትባት ሊሰጥ ነው

 

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 2 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በ10 ቀናት ውስጥ ለ2 ነጥብ 6 ሚሊየን ነዋሪዎች የኮቪድ 19 ክትባት ለመስጠት ዝግጅት መደረጉን የኦሮሚያ ጤና ቢሮ አስታወቀ።

ከህዳር 8 እስከ 17 ቀን 2014 ዓ.ም በዘመቻ የሚሰጠውን ክትባት እድሜያቸው ከ12 አመት በላይ የሆኑ እንደሚወስዱ የቢሮዉ ምክትል ሀላፊ አቶ ግርማ ቦቶሮ ገልጸዋል።

ለዘመቻው መሳካትም በአዳማ ከተማ ለመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎችና ሀላፊዎች የክትባቱ ሂደት ላይ ለሁለት ቀን የሚቆይ ስልጠና እየተሰጠ ይገኛል።

በክልሉ እስካሁን 1 ነጥብ 2 ሚሊየን ሰዎች ክትባቱን የወሰዱ ሲሆን፥ አሁን ክትባቱ በ13 ዞኖችና በ19 የዞን ከተሞች እንደሚሰጥ ተናግረዋል፡፡

በክልሉ ክትባት የሚሰጥባቸው ቦታዎች በትምህርት ቤቶች፣ በህክምና ተቋማት፣ ሰዎች በሚበዙባቸው የኢንዱስትሪ ማዕከላት መሆኑ ታውቋል፡፡ የክልሉ ከተሞችም ክትባቱ ላይ በአግባቡ በመሳተፍ ኮቪድ19ን እንዲከላከሉ ጥሪ አቅርበዋል።

 

በጌታቸው ሙለታ

 

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.