Fana: At a Speed of Life!

በኢትዮጵያ ላይ ተገቢነት የሌላቸው ምንጮች እየተጠቀሱ የፈጠራ ዜናዎች ይሰራሉ -ኢሃም አሊቭ

 

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 2 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) “በኢትዮጵያ ላይ ተገቢነት የሌላቸው ምንጮች እየተጠቀሱ የፈጠራ ዜናዎች ይሰራሉ” ሲሉ የአዘርባጃን ፕሬዚዳንት ኢሃም አሊቭ ገለጹ።

ፕሬዚዳንቱ ከቢቢሲ ጋር ባደረጉት ቆይታ እንዳሉት፤ በአሁኑ ወቅት ኢትዮጵያን በተመለከተ የሚሰሩ ዜናዎች በተገቢው መንገድ ምንጭ የሌላቸው መሆኑን ተናግረዋል  ይህ ጉዳይ እራሱ ቢቢሲን እንደሚመለከት በማስገንዘብ።

በአዘርባጃን የሚዲያ ነፃነት፣ ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲ እንደሌለ እንዲሁም ጋዜጠኞችና ተቃዋሚዎች እስር ቤት  እንደሆኑ በመግለጽ ሰፊ የሚዲያ ሽፋን ቢኖርም ይህንን ሽፋን በመረጃ ምንጭ አስደግፎ ያቀረበ አካል አለመኖሩን ጠቁመዋል።

በአግባቡ ምንጭ የማይጠቀስባቸው መረጃዎች የፈጠራ እንደሆኑ ተናግረዋል።

 

አገራቸው አዘርባጃን 80 ከመቶ የኢንተርኔት ተጠቃሚዎች እንዳሉባትና ይህም የመረጃ ነፃነትን በማስፈን ድርሻ እንዳለው አስገንዝበው፤ ተቃዋሚዎችና የእርዳታ ድርጅቶች በነፃነት እንደሚሰሩም አረጋግጠዋል።

ምዕራባውያን በአዘርባጃን ላይ ያላቸው አመለካከትና ወገንተኝነት የሞላበት ሃሳብ ነው ሲሉ መደመጣቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

በተመሳሳይ ምዕራባውያን “ስለ ሚዲያ ነፃነት የማውራት ሞራል የላችሁም” ያሉትፕሬዝዳንቱ፤ የብዙ አገራትና መሪዎቻቸውን ገመና በማውጣት የሚታወቀው የዊኪሊክስ መስራች የደረሰበትን ሁኔታ አስታውሰዋል።

 

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

 

 

 

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.