Fana: At a Speed of Life!

በአዲስ አበባ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ተጠናቀቀ

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 2 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ባለፉት ቀናት ሲሰጥ የቆየው የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ተጠናቀቀ።

ለፈተናው 36 ሺህ 401 ተማሪዎች የተመዘገቡ ሲሆን ፥ ፈተናውን የወሰዱት ተማሪዎች ቁጥር ግን 35 ሺህ 856 መሆናቸውን የከተማው ትምህርት ቢሮ ምክትል ሀላፊ አቶ ዳኘው ገብሩ ተናግረዋል።

በፈተናው ማጠቃለያም ተማሪዎቹ የደም ልገሳ እና በሀገሪቱ በተፈጠረው ችግር ለተፈናቀሉ ወገኖች የምግብ ነክ እና አልባሳት ድጋፍ አድርገዋል።

ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ያነጋገራቸው ተማሪዎች ባደረጉት ድጋፍ መደሰታቸውን እና ሁሉም ዜጋ ለሀገሩ መረጋጋት መስራት እንዳለበት ጥሪ አቅርበዋል።

መደጋገፉም በተሻለ መቀጠል እንዳለበትም ነው የገለጹት።

በአፈወርቅ አለሙ እና ዘቢብ ተክላይ

አካባቢዎን ይጠብቁ!

ወደ ግንባር ይዝመቱ!

መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.