Fana: At a Speed of Life!

ህዝቡ ለክተት አዋጁ በሰጠው ምላሽ ድል እየተመዘገበ መሆኑ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ህዳር 2፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሰሜን ሸዋ ዞን ህዝብ ለክተት አዋጁ ፈጣን ምላሽ በመስጠት ድል እያስመዘገበ መሆኑን የሰሜን ሸዋ ዞን ሰላምና ደህንነት መምሪያ አስታወቀ።

የመምሪያው ሀላፊ አቶ ዋሲሁን ብርሃኑ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደተናገሩት÷ የክተት አዋጁ ከታወጀ በኋላ በርካታ ወጣቶችና ሚሊሻዎች ወደ ግንባር ዘምተዋል።

ሚሊሻዎችና የፋኖ አባላት በተሰማሩበት ግንባር ከመከላከያና ከልዩ ሀይሉ ጋር ሆነው የሽብር ቡድኑ ላይ ከፍተኛ ኪሳራ እያደረሱና መግቢያ መውጫ እያሳጡት እንደሆነም ተናግረዋል።

የዞኑ ህብረተሰብም በግንባር በመሰለፍ ከሚያደርገው አበርክቶ በተጨማሪ የስንቅ ዝግጅት ላይ በመሳተፍ የደጀንነት ተግባር እየሰራ እንደሆነም ተገልጿል።

በተባበረ ክንድ የአሸባሪውን ህወሓት ዕድሜ ለማሳጠር እየተሰራ መሆኑን የገለጸው መምሪያው፥ አሁንም መዝመት የሚችል ማንኛውም ሰው ወደ ግንባር በመትመም ጠላት ላይ ክንዱን እንዲያሳርፍ ጥሪውን አቅርቧል።

በአሁኑ ወቅት የሰሜን ሸዋን መሬት ለመውረርና ለመዝረፍ በዚያም በዚህም የሚፍጨረጨረው የህወሓትና ሽኔ የሽብር ቡድን መመለሻ አጥቶ ተገቢው እርምጃ እየተወሰደበት መሆኑን መሆኑን የመምሪያ ሀላፊው ገልጸዋል።

በአላዩ ገረመው

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.