Fana: At a Speed of Life!

እየተደማመጥንና እየተባበርን አካባቢያችንን በንቃት እየጠበቅን ነው – የሰንበቴ ከተማ ነዋሪዎች

አዲስ አበባ፣ ህዳር 2፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) እርስ በእርስ በመደማመጥና በመተባበር አካባቢያችንን በንቃት እየጠበቅን ነው ሲሉ የሰንበቴ ከተማ ወጣቶች ገለጹ።
በአማራ ክልል ኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን የሰንበቴ ከተማ ወጣቶች ለኢዜአ እንደገለጹት÷ አካባቢያቸውን በመጠበቅ፣መከላከያን በመደገፍና ወደ ግንባር በመዝመት ለጸጥታ ኃይሉ ደጀንና አጋርነታቸውን እያሳዩ ነው።
ወጣቶቹ ጠንካራ አደረጃጀት በመፍጠርና በመተባበር አካባቢያቸውን ነቅተው ከጠላት እየጠበቁ መሆኑንም ገልጸዋል።
የጅሌ ጥሙጋ ወረዳ ባህልና ቱሪዝም ጽህፈት ቤት ሀላፊ አቶ ጀማል ዑመር ወጣቶች የአካባቢያቸውን ሰላም በማስጠበቅ ረገድ የማይተካ ሚና እያበረከቱ መሆኑን ገልጸዋል።
በተመሳሳይ የአካባቢው ማህበረሰብ ከጸጥታ መዋቅሩ ጋር በመቀናጀት ሰርጎ ገቦችንና የውስጥ ባንዳዎችን የመከላከል ስራ እያከናወነ መሆኑን አንስተዋል፡፡
የኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አህመድ ሀሰን በበኩላቸው የህወሓት የሽብር ቡድን ኢትዮጵያን ለማፍረስ የሚያደርገውን ጉዞ ለመግታት ህብረተሰቡ ተቀናጅቶ እየሰራ መሆኑን ገልጸዋል።

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.