Fana: At a Speed of Life!

አምባሳደር ይበልጣል መገናኛ ብዙሃን ትክክለኛ መረጃ እንዲያደርሱ አሳሰቡ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 2፣ 2014(ኤፍ ቢ ሲ)በሱዳን የኢትዮጵያ አምባሳደር ይበልጣል አዕምሮ መገናኛ ብዙሃን ትክክለኛ መረጃ እንዲያደርሱና በሀሰት መረጃ የሀገርን ሠላምና ደህንነት ለማወክ ከመተባበር እንዲቆጠቡ አሳሰቡ፡፡

በሱዳን የኢትዮጵያ አምባሳደር ይበልጣል አዕምሮ ÷ በካርቱም ተቀማጭ ለሆኑ የሀገር ውስጥ እና ዓለምአቀፍ መገናኛ ብዙሃን የሀገራችንን ወቅታዊ ሁኔታ በተመለከተ ጋዜጣዊ መግለጫ ሠጡ።

አምባሳደሩ ÷ አንዳንድ የዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃን ከዕውነታው የራቀ የፈጠራ መረጃ በማሰራጨት የሀገራችንን ገፅታ ጥላሸት እየቀቡ በመሆኑ ሱዳናውያን እና ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ዕውነታውን እንዲረዱ መረጃ መስጠት አስፈላጊ መሆኑን ተናግረዋል።

አምባሳደሩ በማያያዝም አንዳንድ የአሸባሪው ቡድን አካላት `ህወሓት ወደ አዲስ አበባ እየገሰገሰ ነው` እንዲሁም አዲስ አበባ ከበባ ውስጥ ነች በማለት የሀሰት ፕሮፖጋንዳ በማሰራጨት ውዥንብር እየፈጠሩ ያሉ አካላት መኖራቸውን ተናግረዋል።

እኛ ኢትዮጵያውያን ግን በወሬና በሽብር የሚፈርስ ሀገርና ህዝብ ስለሌለን ኢትዮጵያ በአጭር ጊዜ ሠላሟን ታረጋግጣለች ማለታቸውን በሱዳን ከሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

አንዳንድ መገናኛ ብዙሃንና የተለያዩ አካላት ለዚህ ቡድን ወግነው በመታየታቸውም ማዘናቸውን ገልጸዋል፡፡

መገናኛ ብዙሃንም ትክክለኛ መረጃ እንዲያደርሱ እና በሀሰት መረጃ የሀገርን ሠላምና ደህንነት ለማወክ ከመተባበር እንዲቆጠቡ አሳስበዋል፡፡

በሌላ በኩል አምባሳደሩ ÷የሱዳንን ወቅታዊ ሁኔታን የኢትዮጵያ ሕዝብና መንግስት በቅርበት እንደሚከታተሉ ፤ የሱዳንን ሠላምና ልማት ኢትዮጵያውያን እንደራሳቸው ሠላምና ልማት እንደሚመለከቱ ፤ አሁን ሀገሪቱ የገጠማትን ችግርም ቢሆን ያለማንም ጣልቃ ገብነት ሱዳናውያን በራሳቸው የመፍታት ብቃቱ አላቸው የሚል ጽኑ ዕምነት በኢትዮጵያ መንግስትና ሕዝብ ዘንድ እንዳለም አረጋግጠዋል፡፡

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.