Fana: At a Speed of Life!

በናይጄሪያ ታጣቂዎች በፈጸሙት ጥቃት በትንሹ የ30 ሰዎች ህይወት አለፈ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 3፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በናይጄሪያ ታጣቂዎች በፈጸሙት ጥቃት በትንሹ የ30 ሰዎች ህይወት ማለፉ ተሰምቷል።

በሰሜን ምስራቅ ናይጄሪያ ቡርኖ ግዛት ታጣቂዎች በፈጸሙት ጥቃት በትንሹ የ30 ሰዎች ህይወት ማለፉን የአካባቢው ባለስልጣናት አስታውቀዋል።

ከዚህ ባለፈም ታጣቂዎች ቁጥራቸው በውል ያልታወቁ ህጻናት እና ሴቶችን ጠልፈው መውሰዳቸው ነው የተነገረው።

የቡርኖ ግዛት ቃል አቀባይ አህመድ አብዱራህማን ቡንዲ፥ በአካባቢው የሚንቀሳቀሱት ጽንፈኛ ታጣቂዎች የሰዎችን ህይወት በአሰቃቂ ሁኔታ ከመቅጠፋቸው ባለፈ በንብረት ላይ የከፋ ጉዳት ማድረሳቸውን ተናግረዋል።

በዚህም ቁጥራቸው ከ30 በላይ የሆኑ ተሽከርካሪዎችን እና የተለያዩ መኖሪያ ቤቶችን ማውደማቸው ተገልጿል።

እንደ አይን እማኞች ገለጻ ታጣቂዎች በአካባቢው የነበሩ  ሾፌሮችን እና ረዳቶችን በእሳት አቃጥለው ገድለዋል።

እንዲሁም የአካባቢውን ነዋሪዎች ንብረት በመዝረፍ በርካታ ሱቆችን በእሳት ማጋየታቸው  ነው የተገለጸው።

ይሁን እንጂ ለጥቃቱ እስካሁን ሃላፊነት የወሰደ አካል አለመኖሩ በዘገባው ተመላክቷል።

በሰሜን ምስራቅ ናይጄሪያ ታጣቂዎች ባለፉት አስርት ዓመታት ውስጥ በፈጸሙት ጥቃት የ36 ሺህ ሰዎች  ህይወት ሲያልፍ፥ ከ2 ሚሊየን በላይ የሚሆኑ ዜጎች ደግሞ ከመኖሪያ ቀያቸው ተፈናቅለዋል።

 

ምንጭ፦https://www.france24.

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.