Fana: At a Speed of Life!

የዲጂታል ሉአላዊነት የአንድ አገር ብሄራዊ ሉአላዊነት ጉዳይ መሆኑ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 3፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ የማህበራዊ ትስስር ገጾችን ለማልማት የያዘችው አቋም በቴክኖሎጂው ዘርፍ ነፃ ሀገር መሆኗን ያሳየ ነው ሲል የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ ገለጸ፡፡
የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ሹመቴ ግዛው ÷ የዲጂታል ሉአላዊነት ጉዳይ በዓለም አቀፍ ደረጃ ትልቅ አጀንዳ እየሆነ መምጣቱን ገልጸዋል።
የተቋሞቻችንን የሳይበር ደህንነት ማስጠበቅ ሲቻል የሀገርን ደህንነት ማስጠበቅ ነው ያሉት ዋና ዳይሬክተሩ÷ በሳይበር ምህዳሩ ላይ የሀገርን ሉአላዊነት ማስጠበቅ ደግሞ ለአንድ ቡድን አልያም ተቋም የሚተው ሳይሆን የሁሉም ኃላፊነት መሆኑንም ጠቁመዋል።
ኢትዮጵያ ትልቅ አገር ነች ያሉት ዋና ዳይሬክተሩ፥ ነጻ አገር ሆነን ቆይተናል በቴክኖሎጂው ዘርፍም ነጻነታችንን ማሳየት አለብን ነው ያሉት፡፡
በማህበራዊ ሚዲያ ዘርፍ በራስ አቅም እንዲሁም ከግሉ ዘርፍ ጋር በመቀናጀት እየተሰሩ ያሉ ስራዎች መኖራቸውን እና ውጤት ማስገኘታቸውንም አስታውቀዋል።
ለመጠቀም የደረሱ የተግባቦት ፕላትፎርሞች መኖራቸውን እነዚህም በቅርብ ጊዜ ለህዝብ ይፋ እንደሚሆኑ ጠቅሰው÷እኛ ኢትዮጵያውያን በቴክኖሎጂ አመጣሽ ሽብር አንሸነፍም ሲሉም ተናግረዋል።
የተሻለ ሀሳብ ያላቸው በግልም ይሁን በተለያዩ ተቋማት ውስጥ ያሉ አካላት ወደ ኢንፎርሜሽን መረብ ደኅንነት ኤጀንሲ በመምጣት በጋራ እንዲሰሩ ጥሪ ማቅረባቸውን ከኤጀንሲው ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.