Fana: At a Speed of Life!

በደቡብ ክልል ከ1 ነጥብ 5 ሚሊየን በላይ ዜጎች የኮቪድ19 ክትባት ሊሰጥ ነው

አዲስ አበባ፣ ህዳር 3፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በደቡብ ክልል ከህዳር 10 እስከ 19 ቀን 2014 ዓ.ም ባሉት ቀናት ከ1 ነጥብ 5 ሚሊየን በላይ ዜጎች የኮቪድ-19 ክትባት እንደሚያገኙ የክልሉ ጤና ቢሮ አስታወቀ፡፡
ቢሮው የኮቪድ-19 ክትባት ዘመቻን አስመልክቶ በወላይታ ሶዶ የምክክር መድረክ እያካሄደ ነው።
በመድረኩ ላይ የክልሉ ጤና ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ መና መኩሪያ እንደገለጹት የኮሮና ቫይረስ በዓለም አቀፍ ደረጃ ስጋት ሆኖ በመቆየቱ ህብረተሰቡን በከፍተኛ ጫና ውስጥ እንዲያልፍ አድርጎታል።
ቫይረሱ እያደረሰ ያለውን ጉዳት ለመከላከል አካላዊ ርቀት መጠበቅ፣ አዘውትሮ የእጅ ንጽህናን መጠበቅ፣ የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ማስክ ማድረግ እና ተያያዥ የጥንቃቄ መንገዶችን መተግበር እንደሚገባ ጠቁመዋል።
የኮቪድ-19 ክትባት መከተብ የቫይረሱን ስርጭት ለመከላከል ያስችላል ያሉት አቶ መና÷ ይህንን ተደራሽ ለማድረግ ከህዳር 10 እስከ 19 ቀን 2014 ዓ.ም ባሉት ተከታታይ ቀናት እስከ 1 ነጥብ 5 ሚሊየን የሚደርሱ የህብረተሰብ ክፍሎችን በዘመቻ ለመከተብ መታቀዱን ተናግረዋል።
የክትባት ዘመቻው ስኬታማ እንዲሆን የሚዲያ እና የኮሙኒኬሽ ዘርፉ ለህብረተሰቡ ግንዛቤ በማስጨበጥ ረገድ ሚናውን ሊወጣ ይገባልም ብለዋል።
በምክክር መድረኩ የሀይማኖት አባቶች፣ የሚዲያ እና የኮሙኒኬሽን አስተባባሪዎች ተገኝተዋል መባሉን ከክልሉ ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.