Fana: At a Speed of Life!

ኒውዚላንድ በአፍሪካ ህብረት ለሚደረገው የህዳሴ ግድብ ድርድር ያላትን ድጋፍ ገለጸች

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 3 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ኒውዚላንድ ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብን በተመለከተ በአፍሪካ ህብረት በኩል የሚደረገው ድርድር ውጤት ያመጣል ብላ እንደምታምን በኢትዮጵያ እና አፍሪካ ህብረት የኒውዚላንድ አምባሳደር ሚካኤል አፕተን ገለጹ።
አምባሳደሩ ከውሃና ኢነርጂ ሚኒስትር ዶክተር ኢንጂነር ሃብታሙ ኢተፋ ጋር በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል።
በውይይታቸው ወቅትም ሃገራቸው የህዳሴ ግድብን በተመለከተ በአፍሪካ ህብረት በኩል የሚደረገው ድርድር ውጤት ያመጣል ብላ እንደምታምን እና ይህንም እንደምትደግፍ ገልጸዋል።
በቀጣይ ጊዜም የዜሮ ካርበን ልቀት መጠን ግብን ለማሳካት በአፍሪካ ህብረት በኩል የገንዘብ ድጋፍ ለማድረግ ሃገራቸው ማቀዷን ገልጸው ከዚህ ውስጥ ኢትዮጵያ አንዷ መሆኗን ጠቁመዋል።
የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትር ዶክተር ኢንጂነር ሃብታሙ ኢተፋ በበኩላቸው በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ መሪነት ባለፉት ሁለት አመታት ከ4 ቢሊየን በላይ ችግኞች መተከላቸውን ጠቅሰዋል።
ይህም የአባይ ወንዝን ጨምሮ በሃገሪቱ ያሉ የውሃ አካላትን ደህንነት ለመጠበቅ የሚያስችል መሆኑንም አስረድተዋል።
የህዳሴ ግድብም ለሱዳንና ግብፅ ያለውን ጥቅም ማስረዳታቸውን ከውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
በውይይቱ ወቅት በቀጣይ በጋራ በሚሰሩ የታዳሽ ሀይል ልማት፣ የውሃና ሳኒቴሽን፣ ድርቅ፣ የአካባቢ ጥበቃና እንክብካቤ እንዲሁም የአየር ንብረት ለውጥን በተመለከቱ ጉዳዮች ላይ መክረዋል።
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.