Fana: At a Speed of Life!

በአሰላ ከተማ በህገ ወጥ የንግድ ተቋማት ላይ እርምጃ ተወሰደ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 3 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአሰላ ከተማ በህገ ወጥ መንገድ የንግድ ስራ ሲያከናውኑ በተገኙ 240 ተቋማት ላይ እርምጃ ተወሰደ።
የከተማው ንግድና ገበያ ልማት ፅህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ገነሞ ነገዎ እንደገለፁት፥ 160 የንግድ ተቋማት በህገ ወጥ ንግድተሰማርተው በመገኘታቸው የታሸጉ ሲሆን 80 ለሚሆኑት ደግሞ የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷል፡፡
የንግድ ተቋማቱ ለሚሰሩት ስራ ንግድ ፍቃድ ይዞ አለመገኘት፣ ዋጋ መጨመር እና ደረሰኝ ሳይዙ በመነገዳቸው ምክንያት እርምጃው ተወስዶባቸዋልም ነው ያሉት።
ከዚሁ ጋር በተያያዘም አምስት ግለሰቦች በህግ ጥላ ስር እንዲውሉ ተደርጓል ነው ያሉት የፅህፈት ቤት ሃላፊው፡፡
ህገ ወጦችን የማጥራቱና ወደ ህጋዊ አሰራር የመመለሱ ተግባር በቀጣይ ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም ተናግረዋል፡፡
ተቋማቱ የሚጠበቅባቸውን አሟልተው ከተገኙ ህጋዊ የመስሪያ ፍቃድ ለመስጠት ፅህፈት ቤቱ ዝግጁ መሆኑን ኃላፊው አንስተዋል፡፡
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.