Fana: At a Speed of Life!

ሳዑዲ አረቢያ ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን ግንኙነት ማጠናከር እንደምትፈልግ ገለፀች

 

አዲስ አበባ፣ ህዳር 3፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትር ዶክተር ኢንጂነር ሃብታሙ ኢተፋ በኢትዮጵያ ከሳዑዲ አረቢያ አምባሳደር ሳሚ ጀማል አብደላ ጋር ተወያዩ።

የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትር ዶክተር ኢንጂነር ሃብታሙ ኢተፋ ሳዑዲ አረቢያ ለኢትዮጵያ የውሃውን ዘርፍ ለማገዝ ላደረገችው የ50 ሚሊየን ዶላር የገንዘብ ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል ።

በቀጣይም በውሃና በኢነርጂ ስራዎች አብረው ለመስራት ተስማምተዋል ።

በኢትዮጵያ ከሳዑዲ አረቢያ አምባሳደር ሳሚ ጀማል አብደላ የኢትዮጵያ እና የሳዑዲ አረቢያን ግንኙነት ይበልጥ ለማጠናከር እንደሚፈልጉ ተናግረዋል።

አያይዘውም በማዕድን ምርት የሳዑዲ ኩባንያዎች ወደ ኢትዮጵያ እንዲገቡ እንደሚደረግ ጠቁመው፥ በሳዑዲ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ሁኔታንም በተመለከት ከመንግስት ጋር እንደሚሰሩም አስረድተዋል።

አክለውም በአዲስ አበባ ህይወት እንደቀድሞው መቀጠሉን ጠቁመው “እኔ ከተማ ውስጥ ስንቀሳቀስ እንደሚባለው ያየሁት ውጥረት የለም” ብለዋል።

አምባሳደሩ ከወደ ሰሜን የሚስተዋለው ችግርም መፍትሄ ይገኛል ብለን እናምናለን ማለታቸውን ከውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ሚኒስትሩ ዶክተር ኢንጂር ሃብታሙ ኢተፉ በበኩላቸው÷ በኢትዮጵያ ያለውን ነባራዊ እውነታ ስለተረዱ አመስግነው ሌሎች ጉዳዩን ማራገብ የሚሹና የሃሰት መረጃ የሚያሰራጩ እውንቱን ለመረዳት ቢሞክሩ መልካም መሆኑን ጠቁመዋል።

አካባቢዎን ይጠብቁ!

ወደ ግንባር ይዝመቱ!

መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.