Fana: At a Speed of Life!

ሕፃናትና ወጣቶች አገር ተረካቢ በመሆናቸው እጅ መታጠብን ባህላቸው ሊያደርጉ ይገባል

አዲስ አበባ፣ ህዳር 3 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ሕፃናትና ወጣቶች የነገ አገር ተረካቢ በመሆናቸው እጅ መታጠብን ባህላቸው አድርገው እንዲያድጉ ሁሉም ዜጋ ኃላፊነነቱን እንዲወጣ የጋምቤላ ክልል ጤና ቢሮ አሳሰበ፡፡

ዓለም አቀፍ የእጅ መታጠብ ቀን በዓለም ለ14ኛ ጊዜ በሀገር አቀፍ ደረጃ ደግሞ ለ13ኛ ጊዜ “ነጋችን በእጃችን” በሚል መሪ ሀሳብ በጋምቤላ ከተማ ተከብሯል።

የጋምቤላ ክልል ጤና ቢሮ ኃላፊ ተወካይ አቶ ኡማን ኡጉላ እጅን መታጠብ በቀላል ወጪ የሚደረግ የበሽታ መከላከያ በመሆኑ ህብረተሰቡ እጁን በመታጠብ ራሱንና ብዙዎቹን ከበሽታዎች መታደግ ይቻላል ብለዋል።

በተለይ ሕፃናትና ወጣቶች የነገ አገር ተረካቢ በመሆናቸው እጅን መታጠብን ባህላቸው አድርገው እንዲያድጉ ሁሉም ዜጎች ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ አሳስበዋል።

በክልሉ ጤና ቢሮ የዋን ዋሽ ፕሮግራም ባለሙያ አቶ ታገሰ ፍቅሬ በበኩላቸው፥ በዓሉ በተላላፊ በሽታዎች የሚደርሰውን የሕፃናትና ሴቶች ሞት ለመቀነስ ለህብረተሰቡ ግንዛቤ በማስጨበጥ ራሱንና ቤተሰቡን ከበሽታዎች ለመጠበቅ እንደሚከበር ተናግረዋል ።

በትምህርት ቤት ያሉ ሕፃናት እጃቸውን መታጠብ ማለት በሽታን ለመከላከል ክትባት እንደመውሰድ ማለት እንደሆነ ማስገንዘብ ያስፈልጋል ማለታቸውን የጋምቤላ ፕሬስ ሴክሬታሪያት ፅህፈት ቤት መረጃ ያመላክታል።

አካባቢዎን ይጠብቁ!

ወደ ግንባር ይዝመቱ!

መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.