Fana: At a Speed of Life!

የአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ለህልውና ዘመቻው ከ7 ሚሊየን ብር በላይ ሃብት አሰባሰበ

 

አዲስ አበባ፣ ህዳር 3፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 4 አስተዳደር ለህልውና ዘመቻው የሚሆን ከ7 ሚሊየን ብር በላይ ሃብት በማሰባሰብ አስረከበ፡፡

የወረዳው አስተዳደር ለህልውና ዘመቻው ከ10 ሚሊየን ብር በላይ ለማሰባሰብ አቅዶ እስካሁን 6 ሚሊየን ብር የሚገመት ደረቅ ሬሽን፣ 1 ሚሊየን ብር በጥሬ ገንዘብ በአጠቃላይ 7 ሚሊየን ብር የሚገመት ሃብት በማሰባሰብ ማስረከብ መቻሉን የወረዳው ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ዳዊት ብርሃኑ ተናግረዋል፡፡

የክፍለ ከተማው ዋና ስራ አስፈፃሚ ወይዘሮ ሽታዬ መሃመድ በበኩላቸው÷ እየተደረገ ያለው የህልውና ዘመቻ ህዝባዊ በመሆኑ እያንዳንዱ ሰው አካባቢውን ከመጠበቅ ጀምሮ ድጋፍ ማድረግ ይገባል ብለዋል፡፡

አሁን የገጠመን ፈተና የህልውና ጉዳይ ነው ያሉት የክፍለ ከተማው የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ አስተባባሪ አቶ ብርሃኑ አበራ ችግሩን በተባበረ ክንድ በአጭር ጊዜ መቀልበስ ይገባል ማለታቸውን ከክፍለ ከተማው ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.