Fana: At a Speed of Life!

የመንግስት የስራ ሀላፊዎች ጉዳት ለደረሰባቸው የሠራዊት አባላት ድጋፍ አደረጉ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 3፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ከተለያዩ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች የተውጣጡ የመንግስት የስራ ሀላፊዎች በህግ ማስከበርና በህልውና ዘመቻው ላይ ጉዳት ለደረሰባቸው የሠራዊት አባላት 2 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር ድጋፍ አደረጉ ።

በቢሾፍቱ የመከላከያ ኮምፕሪሔንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል እና በመከላከያ ዋር ኮሌጅ በመገኘት ከ2 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር በላይ ግምት ያለው ምግብ ነክና ምግብ ነክ ያልሆኑ ቁሳቁስ ድጋፍ ያስረከቡት የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ኤርጎጌ ተስፋዬ ፣ የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ ፣ የፕላንና ልማት ሚኒስትር ዶክተር ፍፁም አሰፋ እንዲሁም የጉምሩክ ኮሚሽነር ደበሌ ቃበታ እና ሌሎች የመንግስት የስራ ሀላፊዎች ናቸው።

ዶክተር ኤርጎጌ ተስፋዬ ለመከላከያ ሰራዊቱ እና ለመላው የፀጥታ ኃይሎች የሚደረገው ድጋፍ አገርን ለማፍረስ ለታደጉ ጀግኖች የተደረገ መሆኑን ገልጸው ፣ይህ አይነቱ የተቀናጀ የተቋማት ድጋፍና ትብብር ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።

በዘመቻው የአካል ጉዳት የደረሰባቸውን የሰራዊት አባላት ህክምና አሰጣጥ አስመልክቶ ማብሪሪያ የሰጡት የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ በበኩላቸው፥ ከመከላከያ ሠራዊቱ የጤና ሙያተኞች በተጨማሪ ከተለያዩ ተቋማት የተውጣጡ ሐኪሞችም ተመድበው አገልግሎት እየሰጡ ናቸው ብለዋል።

በጦርነቱ ምክንያት ጉዳት ለደረሰባቸው የፀጥታ አካላት የሚደረገው ድጋፍ ቀጣይነት ያለው መሆኑን የጉምሩክ ኮሚሽን ኮሚሽነር ደበሌ ቃበታ ተናግረዋል፡፡

የመከላከያ ኮምፕሪሔንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ዋና አዛዥ ብርጋዴር ጀኔራል ተገኝ ለታ፥ ድጋፉን ላደረጉ ተቋማት ምስጋና ማቅረባቸውን ከመከላከያ ሰራዊት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.