Fana: At a Speed of Life!

የደረሱ ሰብሎችን ብክነት ለመቀነሰ መስራት እንደሚገባ ተገለፀ

 

አዲስ አበባ፣ ህዳር 3 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የደረሱ ሰብሎችን ብክነት በቀነሰ መልኩ መሰብሰብ ላይ ትኩረት ተሰጥቶት ሊከናወን እንደሚገባ የግብርና ሚኒስቴር ገለፀ፡፡

በ2013/14 ምርት ዘመን የመኸር ወቅት እርሻ ስራ ከ12 ነጥብ 77 ሚሊየን ሄክተር በላይ መሬት በዘር በመሸፈን ከ374 ነጥብ 66 ሚሊየን ኩንታል በላይ ምርት ለመሰብሰብ ታቅዶ እየተሰራ እንደሚገኝ ተገልጿል፡፡

የደረሱ ሰብሎችን ምርት ያለብክነት እንዲሰበሰብ በየደረጃዉ የሚገኙ የዘርፉ አመራሮችና ባለሙያዎች አርሶአደሮችን በማስተባበር ርብርብ እያደረጉ ይገኛሉ ነው የተባለው፡፡

በዚህም በአብዛኛው የሚሰበሰበው በሰው ጉልበት በመሆኑ እያንዳንዱ አርሶ አደር የራሱና የቤተሰቡን ጉልበት በማስተባበርና ከሌሎች አርሶ አደሮች ጋር ቅንጅት በመፍጠር ቀድመዉ የደረሱ ሰብሎች የድርቀት መጠናቸዉን በመጠበቅ ብክነትን በቀነሰ መልኩ መሰብሰብ ላይ መረባረብ፣እስከሚወቃ በማሳ የሚከመሩ ሰብሎች ሲኖሩ ክምሮች በተለያዩ ተባዮች፣ እንሰሳት እና ወቅቱን ያልጠበቀ ዝናብ ቢከሰት ብክነት እንዳይደርስባቸዉ በጥንቃቄ መከመርና የተለያዩ የመከላከያ ዘዴዎችን መጠቀም እንደሚገባ ተገልጿል፡፡

እንዲሁም የግብርና ሚካናይዜሽን መጠቀም በሚቻልባቸዉ አካባቢዎች የምርት መሰብሰቢያ ማሽኖችን በሰፊዉ በመጠቀም መሰብሰብ እንዲቻል አገልግሎት ሰጪዎችንና ተጠቃሚው በማገናኘትና አርሶአደሩን በማደራጀት ጊዜን በአግባቡ ለመጠቀም እንዲቻል አመራሩና ባለሙያዎች በትኩረት ሊመሩት ይገባልም ነው የተባለው፡፡

አሸባሪዉን የህወሓት ቡድን ለመፋለም ወደ ህልዉና ዘመቻዉ የተቀላቀሉ አርሶአደሮችን ሰብልም ቅድሚያ ሰጥቶ በጋራ በመሰብሰብ ለቤተሰቦቻቸዉ አስፈላጊዉን ድጋፍ መስጠት ቀዳሚ ትኩረት መስጠት ያስፈልጋል መባሉን የግብርና ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.