Fana: At a Speed of Life!

ሰላምና ፀጥታን ከመጠበቅ ጎን ለጎን የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ እየተሰራ ነው – አቶ ሙስጠፌ ሙሀመድ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 3፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በሶማሌ ክልል ርዕሠ መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ መሀመድ የተመራና የክልሉን ካቢኔ ያካተተ ልዑክ በሸቤሌ ዞን የመስክ ጉብኝት አድርጓል፡፡
ልዑኩ በዞኑ በተለይም በቤር አኖ ወረዳ የዋቢ ሸቤሌ ወንዝን በመጠቀም በመስኖ የለማ 475 ሄክታር ሰብል የጎበኘ ሲሆን፥ ከዚህ በፊት ትኩረት ያልተሰጠው የመስኖ ሥራ አሁን ላይ ከፍተኛ ውጤት እያስመዘገበ መሆኑ ተገልጿል።
በክልሉ በሸቤሌ ወንዝ እየለማ የሚገኝ መሬት ላይ የሚመረቱትን የግብርና ምርቶች በአነስተኛ ዋጋ ለሀገር ውስጥ ገበያ በማቅረብ በሀገሪቱ በምግብ እራስን ለመቻልና የውጭ ሀገር ጫናን ለመቋቋም በስፋት በመሠራት ላይ መሆኑም በጉብኝቱ ወቅት ተጠቁሟል።
የሶማሌ ክልል ርዕሠ መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ መሀመድ መንግሥት የክልሉ ህዝብ ሙሉ ለሙሉ በአርብቶ አደርነት እንዳይወሰንና በግብርና በተለይ ለእርሻ ሥራ ትኩረት እንዲሰጥ ይሰራል ማለታቸውን የሶማሌ ክልል መገናኛ ብዙኃን ዘግቧል፡፡
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.